የቀድሞ የጋና ብሄራዊ ቡድን ኮከብ ያኩቡ አቡበከር በ36 አመቱ ህይወቱ አለፈ

Image result for Yakubu Abubakar GHANA

ለጥቋቁር ኮከቦቹ በአፍሪካ ዋንጫ እና በአለም ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ መሳተፍ የቻለው ጋናዊው የአማካይ ተከላካይ ያኩቡ አቡበከር ህይወቱ አለፈ፡፡

ለጋና ብሄራዊ ቡድን 16 ጨዋታዎችን ማድረግ የቻለው የአማካይ ተከላካዩ ማክሰኞ በ ደቡብ ጋና በምትገኘው ቴማ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ቢታከምም ህይወቱን ማትረፍ ሳይቻል ቀርቷል፡፡

የጋና እግር ኳስ ማህበር የተጫዋቹን ህልፈት ተከትሎ የተሰማውን ሀዘን በይፋዊ የቲውተር ገጹ ያሳወቀ ሲሆን በተጫዋቹ ሞት ላዘኑት ቤተቦቹ እና አድናቂዎቹ መጽናናትን ተመኝቷል፡፡ ያኩቡ አቡበከር ለጋና ብሄራዊ ቡድን ከታዳጊው እስከ ዋናው ቡድን መጫወት የቻለ ሲሆን በ2006 አስደናቂ የአለም ዋንጫ ጉዞን ማድረግ የቻለው የጋና ብሄራዊ ቡድን አባል ነበር፡፡

በታላቁ የሆላንድ ክለብ አያክስ አምስተርዳም ተጫውቶ ያለፈው ያኩቡ አቡበከር በደች ሊግ ቆይታው ለ2 ጊዜያት ያህል ከአያክስ አምስተርዳም ጋር የሊጉን ዋንጫ ከፍ ማድረግ ችሏል፡፡ ለአያክስ አምስተርዳም 89 ጨዋታዎች ላይ የተሰለፈው የቀድሞ የጋና ብሄራዊ ቡድን ኮከብ ለሌላኛው የሆላንድ ክለብ ቪትስ አርሀም ለአምስት አመታት መጫወት ችሏል፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s