የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ቅድመ ቅኝት

በሳምንቱ አጋማሽ ከሚደረጉ የሁለት ቀናት የጨዋታ መርሃግብሮች መካከል አንዱ በሆነው የዛሬ (ረቡዕ) የሻምፒንስ ሊግ ጨዋታዎች በሁለት የተለያዩ የጨዋታ ሰዓቶች ይከናወናሉ። ኢትዮአዲስ ስፖርትም ምሽት ከሚደረጉት ስምንት ጨዋታዎች አበይት ያለቻቸውን ጨዋታዎች መርጣ ስለጨዋታዎቹ ሊያውቋቸው ይገባሉ ያለቻቸውን መሰረታዊ ጉዳዮች እንደሚከተለው ቃኝታለች።

ቶተንሃም ከ ሪያል ማድሪድ

ብዙዎች ቶተንሃም በሻምፒዮንስ ሊጉ የምድብ ማጣሪያ ችግር እንደሚገጥመው ቢጠብቁም ዶርትሙንድን እና አፖል ኒኮሲያን በመርታት በተመሳሳይ ነጥብ ምድቡን ከሪያል ማድሪድ ጋር በጋራ በመምራት አስደናቂ ብቃት እያሳየ ይገኛል። ከዚነዲን ዚዳኑ የአምናው ሻምፒዮን ሪያል ማድሪድ ጋር በሚያደርገው በዛሬ ምሽቱ የዌምብሌይ ጨዋታም የምድቡን መሪነት ለብቸኝነት ለመቆጣጠር ውጥን ይዞ እንደሚጫወት ይጠበቃል።

የሁለቱ ቡድኖች የእርስበእርስ ግንኙነት

ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው አራት ጨዋታዎች ሪያል ማድሪድ በሶስቱ ድል ሲያደረግ በአንዱ ደግሞ በአቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የሁለቱ ቡድኖች ቁጥራዊ መረጃዎች

ሪያል ማድሪድ በዚህ የውድድር ዘመን ከሜዳው ውጪ ባደረጋቸው ጨዋታዎች 88 በመቶውን አሸናፊ ሲሆን ከእነዚህም ቢያንስ ሁለት ግቦችን ከመረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል። በ25 በመቶ ጨዋታዎቹ ላይ ደግሞ መረቡን አላስደፈርም።

የቡድኖቹ ዜናዎች 

ቶተንሃም

በስፐርሶች በኩል ቪክቶር ዊንያማ አሁም በጉዳት ምክኒያት በዚህ ጨዋታ ላይ የማይሰለፍ ቢሆንም ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ የቋንጃ ጉዳት ገጥሞት የነበረው ሃሪ ኬን ለዚህ ጨዋታ ወደሜዳ እንዲመመለስላቸው ተስፋ ሰንቀዋል። እንዲሁም ዴሌ አሌ ተጥሎበት ከነበረው የሶስት ጨዋታዎች እገዳ የሚመለስላቸው ሌላኛው ወሳኝ ተጫዋቻቸው ነው። 

ሪያል ማድሪድ

ግብ ጠባቁው ኬይሎር ናቫስ፣ ተከላካዩ ዳኒ ካርቫኻል፣ አማካኙ ማቲዮ ኮቫቺች እና አጥቂው ጋርዝ ቤል በረቡዕ ምሽቱ ጨዋታ በሪያል ማድሪድ በኩል ሊሰለፉ የማይችሉ ተጫዋቾች ናቸው።

ናፖሊ ከ ማንችስተር ሲቲ


የምሽቱ ጨዋታ ለናፖሊ የሞት ሽረት ጨዋታ ነው። በምድቡ በሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ናፖሊ ለለው የዚህ ምድብ ጨዋታ በአቻ ውጤት የሚተናቀቅ ከሆነ ቢያንስ ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ያስችለዋል። ነገር ግን የሴሪ ኣው ቡድን በሁሉም ውድድሮች ላይ ካደረጋቸው ያለፉት 10 ጨዋታዎች ስምንቱን በማሸነፍ የሻምፒዮን ሊጉ የጥሎ ማለፍ ማጣሪያ ለመቀላቀል መፋለም የሚያስችለው ብቃት ላይ የሚገኝ መሆኑም ከምድቡ መሪ እና የፕሪሚየር ሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ በአምስት ነጥቦች የሚመራውን ማንችስተር ሲቲ ጋር በሚያደረገው ጨዋታ ሊያስመሰክር የሚችልበት ዕድል አለው።

የሁለቱ ቡድኖች እርስበርስ ግንኙነት

ናፖሊ እና ማንችስተር ሲቲ ከዚህ ቀደም ተገናኝተው ባደረጓቸው ጨዋታዎች አንድ አንድ ተሸናንፈው አንድ ጨዋታ ላይ ደግሞ በእቻ ውጤት ተለያይተዋል።

የናፖሊና የማንችስተር ሲቲ ቁጥራዊ መረጃዎች

ማንችስተር ሲቲ በዚህ የውድድር ዘመን ከሜዳው ውጪ ባደረጋቸው ጨዋታዎች መቶ በመቶ ማሸነፍ የቻለ ሲሆን በእነዚህ ጨዋታዎች ላይም በአማካኝ ሶስት ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል። በሌላ በኩል ናፖሊ በዚህ የውድድር ዘመን በሜዳው ያደረጋቸውን 84 በመቶ ጨዋታዎች ድል ማድረግ ሲችል በየጨዋታዎቹ ያስቆጠሯቸው አማካኝ ግቦቹም ሁለት ናቸው።

የቡድኖቹ ዜናዎች

ናፖሊ

ተከላካዩ ሎሬንዞ ቶነሊ እና አጥቂው አርካዲዩዝ ሚሉክ በናፖሊ በኩል የማይስለፉ ተጫዋቾች ናቸው።

ማንችስተር ሲቲ

ሁለቱ የተከላካይ ክፍል ተጣማሪዎች ቪንሰንት ኮምፓኒ እና ቤንጃሚም ሜንዲ አሁንም በማንችስተር ሲቲ የጉዳት ችግር እንደሆኑ ይቀጥላሉ።

ሊቨርፑል ከ ማሪቦር

የሊቨርፑል በሻምፒንስ ሊጉ ላይ የሚኖረው ቆይታ በምድብ ማጣሪያው የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎችን በአቻ ውጤት ማጠናቀቁን ተከትሎ አጠራጣሪ ሆኖ ቢቆይም፣ ነገር ግን ማሪቦርን ከሜዳው ውጪ 7ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የደበዘዘውን ተስፋውን ማለምለም ችሏል። በዛሬ ምሽቱ ጨዋታም የስሎቫኒያውን ቡድን በአንፊልድ በመገጠም ወደቀጣዩ ዙር ለማለፍ የሚያደረገውን ጥረት ከፍ ለማደረግ ውጥን ይዞ ይጫወታል። ከምድቡ ክለቦች ጋር ባደረጋቸው ሁሉም ጨዋታዎች ሽንፈት የደረሠበት ማሪቦር በእጅጉ ጠባብ የሆነ የማለፍ ተስፋ ይዞ ይህን ጨዋታ የሚያደረግም ይሆናል።

የሁለቱ ቡድኖች የእርስበርስ ግንኙነት

ሊቨርፑል 7ለ0 በሆነ ውጤት መርታት የቻለበት ጨዋታ ከዚህ ቀደም በሁለቱ ክለቦች መካከል የተደረገ ብቸኛ ጨዋታ ነው።

የሊቨርፑልና ማሪቦር ቁጥራዊ መረጃዎች

ሊቨርፑል በዚህ የውድድር ዘመን በሜዳው ባደረጋቸው ጨዋታዎች 57 በመቶ በድል ሲያጠናቅቅ ማሪቦሮ ደግሞ በሻምፒዮን ሊጉ ከሜዳው ውጪ ባደረጋቸው ሰባት ጨዋታዎች 72 በመቶ ሽንፈት ደርሶበታል። በ57 በመቶዎቹ ላይ ደግሞ በትንሹ ሶስት ግቦች ተቆጥረውበታል።

የቡድኖቹ ዜናዎች

ሊቨርፑል

ሊቨርፑል ደያን ሎቭረንን፣ ዳኒ ዋርድን፣ አዳም ላላናን፣ ሳዲዮ ማኔን፣ አዳም ቦጃንን እና ናትናኤል ክላይንን በጉዳት ምክኒያት በዚህ ጨዋታ የማያሰልፍ ሲሆን፣ ፊሊፔ ኮቲኒሆም መሰለፉ አጠራጣሪ ነው።

ማሪቦር

የመሃል ተከላካዩ ዴኒስ ስሜብ እና አጥቂው ሉኬ ዛሆቪች በእንግደው ክለብ በኩል በጉዳት ላይ የሚገኙ ተጫዋቾች ናቸው።

በሌሎች የምሽቱ ጨዋታዎች ቤሽኪታሽ ሞናኮን ምሽት 1፡00 ላይ ሲገጥም፣ ሲቪያ ከስፓርታክ ሞስኮ፣ ሻካታር ዶነተስክ ከፌይኖርድ፣ ፖርቶ ከአርቢ ሌፕዢግ፣ ዶርትሙንድ ከአፖል ኒኮሲያ በተመሳሳይ 3፡45 የሚጫወቱ ይሆናል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s