“ጃክ ዊልሻየር ለእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን የመጫወት አቅም አለው”- አርሰን ዌንገር

Wilshere is expected to start Thursday night's Europa League game against Red Star Belgrade

የአርሰናሉ አለቃ አርሰን ዌንገር የቡድናቸው የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ጃክ ዊልሻየር በአንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ስብስብ ውስጥ መካተት እንዳለበት ተናገሩ፡፡ ፈረንሳዊው እንዳሉት ከሆነም እንግሊዛዊው ኢንተርናሽናል በሙሉ አቋሙ ላይ መገኘቱን ተከትሎ የሶስቱ አናብስት አሰልጣኝ ጋሬት ሳውዝጌት ጥሪ እንዲያቀርቡለት መልዕክታቸውን አስተላለፈዋል፡፡

የአርሰናሉ አማካይ ከሁለት አመታት በፊት ደርሶበት በነበረው የእግር ስብራት ምክንያት ለወራት ከሜዳ መራቁን ተከትሎ የቀድሞ ድንቅ ብቃቱን ማሳየት ተስኖት ባሳለፍነው አመት ለቦርንማውዝ በውሰት ከተሰጠ በኋላ በመድፈኞቹ ቤት ዳግም ተመልሶ በአዲሱ የውድድር ዘመን መልካም እንቅስቃሴን እያደረገ ይገኛል፡፡

በተለይም አርሰናል ሬድ ስታር ቤል ግሬድን በረታበት የኢሮፓ ሊግ ጨዋታ ላይ ተሰፋ ሰጪ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴን ማሳየቱን ተከትሎም ከወዲሁ በበርካቶች እየተወደሰ ይገኛል፡፡ ይህንን ተከትሎም የአርሰናሉ አለቃ አርሰን ዌንገር “ሳስበው አሁን ለሀገሩ ለመጫወት ዝግጁ ነው በአሁኑ ሰዓት በሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛል ” በማለት ጃክ ዊልሻየር ወደ ብሄራዊ ቡድኑ ጥሪ ሊደረግለት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የእንግሊዝ በወርሀ ህዳር መጀመሪያ ከብራዚል እና ጀርመን ብሄራዊ ቡድን ጋር በምታደርጋቸው 2 የወዳጅነት ጨዋታዎች ላይ የሚሳተፉ ተጫዋቾቿን የፊታችን ሀሙስ ይፋ የምታደርግ ሲሆን አሰልጣኝ ጋሬት ሳውዝጌትም ከረጅም ጊዜያት በኋላ ለእንግሊዛዊው አማካይ ጃክ ዊልሻየር ጥሪ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s