ሰይዶ ማኔ ወደ ልምምድ ተመልሷል

Sadio Mane made his return to full Liverpool training on Thursday

ሴኔጋላዊው የሊቨርፑል የመስመር አጥቂ ሰይዶ ማኔ ከቋንጃ ጉዳቱ አገገሞ ልምምድ ጀመረ፡፡ ሀገሩ ሴኔጋል በአፍሪካ ዋንጫ ኬፕቨርዴን በገጠመችበት ጨዋታ ላይ ጉዳት የገጠመው የመስመር አማካዩ ለስድስት ሳምንታት ከሜዳ ከራቀ በኋላ ዛሬ በሜልውድ የልምምድ መሃከል በመገኘት ልምምዱን ከውኗል፡፡

በጉዳት ላይ እያለ ከሴኔጋል ብሄራዊ ቡድን ጥሪ የደረሰው ሰይዶ ማኔ ሊቨርፑል የፊታችን ቅዳሜ ከዌስትሀም ጋር በሚያደርገው የሊጉ 11ኛ ሳምንት ጨዋታ ላይ እንደሚሰለፍ የሚጠበቅ ሲሆን ከ1 ሳምንት በኋላም ሴኔጋል በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በምታደርጋቸው 2 ወሳኝ ጨዋታዎች ላይ ለሀገሩ እንደሚሰለፍ ተነግሯል፡፡

 

ሰይዶ ማኔ በሊጉ ጅማሮ ለቀዮቹ አስደናቂ ብቃቱን በማሳየት በ5 ጨዋታ 3 ግቦችን በማስቆጠር የአመቱን ጅማሮ መልካም ቢያደርግም በኢትሀድ ሊቨርፑል ከማንችስተር ሲቲ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ላይ ቀይ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ የ3 ጨዋታ እገዳ በሊጉ ከተጣለበት በኋላ የደረሰበት ጉዳት ቀዮቹን በሚገባ እንዳያገለግል እንቅፋት ሆኖበት መቆየቱ ይታወሳል፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s