በአዲስ አበባ ስቴዲየም የሚደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ተራዝመዋል

 

picsart_09-24-04-52-012ለ4 ጊዜያት ከተራዘመ በኋላ የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ ጅማሮውን የሚያደርገው የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች መኃከል በአዲስ አበባ ስቴዲየም የሚደረጉ 3 መርሀ ግብሮች  መተላለፋቸው ተነግሯል፡፡

ቅዳሜ ጥቅምት 25 መከላከያ ከኢትዮ አሌክትሪክ እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና እና መከላከያ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የቻን የማጣሪያ ጨዋታ ምክንያት የተሰረዘ ሲሆን በተመሳሳይ የፊታችን እሁድ እንዲካሄድ ቀነ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የድሬዳዋ ከተማ ጨዋታም በቻን የማጣሪያ ጨዋታ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ የተላለፈ ጨዋታ ነው፡፡

ሆኖም በክልል ከተሞች ላይ የሚደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ቅዳሜ እና እሁድ ቀጥለው የሚካሄዱ ሲሆን በዚህም መሰረት  ወልዲያ ከ አዳማ ከተማ ፣ አርባምንጭ ከተማ ከ መቐለ ከተማ እንዲሁም  ጅማ አባ ጅፋር ከ ሀዋሳ ከተማ የፊታችን ቅዳሜ በ9 ሰዓት የሚካሁዱ ጨዋታዎች ሲሆኑ

እሁድ ጥቅምት 26 ደግሞ ወልዋሎ አዩ. ከ ፋሲል ከተማ በአዲግራት ከተማ ላይ ከቀኑ በ9 ሰዓት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ ሊጉ ሰኞ ሲቀጥል  ደደቢት እና  ወላይታ ድቻ አዲስ አበባ ስታድየም አመሻሽ 11፡30  ላይ በሊጉ 1ኛ ሳምንት የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s