የቀድሞው የቡንደስሊጋ ተጫዋች የሎተሪ አሸናፊ ሆነ

የቀድሞው የቡንደስሊጋ ተጫዋች ቶሚ ቤችማን በቅርቡ ከፕሮፌሽናል እግርኳስ እራሱን ካገለለ አንደ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በዴንማርክ የሎተሪ ዕጣ ሽልማት ዕድለኛ መሆን ችሏል።

በጀርመን ከፈተኛው ሊግ ላይ ለሚጫወተው ቦኸም ክለብ 82 ጨዋታዎችን አድርጎ 13 ግቦችን ከመረብ ላይ ማስረፍ የቻለው የ35 ዓመቱ አጥቂ አምስት ሚሊዮን ክሮን (20,983,950 አከባቢ የሚሆን ብር) ሽልማቱን ሲቀበል ከቤተሰቦቹ ጋር የእርፍት ጊዜውን በማሳለፍ ላይ ይገኝ ነበር።

እንደምንጊዜውም ሁሉ ቤችማን የሎተሪ ቁጥሩን ለመቁረጥ የተጠቀመው የልጁን ልደት ቀን ነበር። ነገር ግን ከዚህ ቀደም ብዚህ ቁጥር ማሸነፍ የቻለው በመጠኑ አነስተኛ የሆነ ገንዘብ ነበር። 

“የላኪውን አድራሻ ስመለከተው ከዚህ በፊት 50 ክሮን እንዳሸነፍኩ ከተገለፀለኝ ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ አረጋገጥኩ።” ሲል ተጫዋቹ ዴንማርኩ ጋዜጣ ኢክስትራብላዴት ተናግሯል።

“ለዳንስክ ስፒል [የሎተሪው ድርጅት] ደወልኩ። ከዚያም ዜናውን ራሳቸው አረጋገጡልኝ።

“የፀደይ ወቅት የእረፍት ጊዜ መዝናኛ ጊዜያችን ምናልባትም ካቀደውም በላይ የተቀናጣ ሊሆን ይችላል።” ሲል የቀድሞው ተጫዋች የአሁኑ የሎተሪ ዕጣ ዕድለኛው ተናግሯል።

ቤችማን በጀርመን ከቦኸም በተጨማሪ ለፍሪበርግም ተጫውቷል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s