“የእኔ ቁጥራዊ መረጃ እኔ አልናገረውም ራሳችሁ ‘የክርስቲያኖ ግቦች’ ብላችሁ ወደጉግል ሂዱ” – ሮናልዶ

የሪያል ማድሪዱ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ትችት እየሰነዘሩበት ለሚገኙ ጋዜጠኞች ያስቆጠራቸውን ግቦች ጉግል ላይ ፈልገው ማግኘት እንደሚችሉ በማስታወስ ለላ ሊጋው ኃያል ክለብ ዳግመኛ መፈረም እንደማያስፈልገው ገልፅዋል።

ሮናልዶ ከሽንፈት መታደግ ባያስችለውም ረቡዕ ምሽት በሻምፒዮንስ ሊጉ በቶተንሃም 3ለ1 በሆነ ውጤት ሽንፈት ለደረሰበትና ካለፈው ዓመት ጥር ወር ወዲህ በተከታታይ ሽንፈት ሲገጥመው የመጀመሪያው ለሆነው ማድሪድ ግብ ማስቆጠር  ችሎ ነበር። 

ፖርቱገላዊው ተጫዋች በዚህ የውድድር ዘመን በ12 ጨዋታዎች ላይ ስምንት ግቦችን ከመረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል። ነገር ግን ማድሪድ ባርሴሎናን በስምንት ነጥቦች ዝቅ ብሎ በሚከተልበት የላ ላሊጋው ውድድር ላይ ካደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች ማስቆጠር የቻለው ግን አንድ ግብ ብቻ ነው። 

ሮናልዶ ግብ በማስቆጠር ላይ በጣም ትኩረት እየተደረገ እንደሆነ ተናግሮ ነገር ግን ያንንም ቢሆን ግን እሱ በርካታ ጊዜያት ማድረግ ስለመቻሉ ተቺዎቹን አስታውሷል።

“በእጅጉ የተረጋጋሁ ሰው ነኝ። ዛሬ ጥሩ ብቃት ማሳየት በእናንተ ዘንድ ከቁጥር አይገባም። የሚቆጠርላችሁ ግብ፣ ግብና ግብ ብቻ ነው።” ሲል ከጨዋታው በኋላ ለጋዜጠኞ ተናግሯል።

“ስለእኔ ቁጥራዊ መረጃዎች እኔ አልነግራችሁም። ራሳችሁ ‘የክርስቲያኖ ሮናልዶ ግቦች’ ብላችሁ ወደጉግል ሂዱ። ሁሉንም በዚያ ታገኛላችሁ። ያ እኔ ፈፅሞ አያስጨንቀኝም።”

ሮናልዶ በማድሪድ እ.ኤ.አ. እስከ2021 ድረስ የሚያቆየው ኮንትራት አለው። ነገር ግን የ32 ዓመቱ ተጫዋች አዲስ ስምምነት ለማድረግ እያጤነበት ስለመገኘቱ ግን አስተያየቶች እየተሰጡ ይገኛሉ።

ይሁንእንጂ ኮከቡ የፊት ተጫዋች “እኔ በጣም ደህና ነኝ። ዳግም መፈረም አያስፈልገኝም።

“አሁንም ድረስ [ቀሪ] አራት የኮንትራት ዓመታት አሉኝ። ዳግመኛ መፈረም አያስፈልገኝም።” ሲል አክሎ ተናግሯል።

Advertisements
Posted in Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s