ሳንቲ ካዞርላ እግሩን ሊያሳጣው ተቃርቦ የነበረ ጉዳት አጋጥሞት እደነበር ተናገረ

 

32.jpg

የአርሰናሉ አማካይ ሳንቲ ካዞርላ ጉዳቱ ወዳልተፈለገ ደረጃ ደርሶ እግሩን ሊያጣው ተቃርቦ እንደነበረ አሳወቀ፡፡

የስፔኑ ማርካ የዛሬ(አርብ) እትሙ የፊት ገጽ ላይ የሳንቲ ካዞርላ እግር የያዘ ምስል ይዞ ወጥቷል፡፡ተጫዋቹ ከሜዳ ከራቀ ረጅም ወራቶች የተቆጠሩ ሲሆን ጉዳቱም ቀላል የሚባል እንዳልነበረ ከማርካ ጋዜጣ ጋር ያደረገው ቆይታ ላይ አስረድቷል፡፡

የቀድሞ የቪላሪያል ተጫዋች የነበረው ስፔናዊው ተጫዋች ሁለት ጊዜ ተረከዙ ላይ ባጋጠመው ጉዳት ወደ ሜዳ ለመመለስ የተቸገረ ሲሆን በተለይ የሁለተኛ ጉዳቱ ወዳልተፈለገ ኢንፌክሽን ተቀይሮ እግሩን ሊያሳጣው ተቃርቦ እንደነበር አሳውቋል፡፡

ካዞርላ ጉዳቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ካጋጠመው በኋላ ለስምንት ያህል ጊዜ ቀዶ ጥገና ያደረገ ሲሆን ቁስሉንም ለመሸፈን ከክንዱ ላይ ቆዳ ማንሳት እስከመድረስ ተደርሷል፡፡ከስፔኑ ማርካ ጋርም ቆይታ ያደረገው ካዞርላ “ዶክተሮች ከልጆቼ ጋር በመናፈሻዮ ዳግም መራመድ የምችል ከሆነ እድለኛ አንደምሆን ነግረውኝ ነበር፡፡ችግሩ የከፋና ቁስሉ በመመረዙ በድጋሚ ይከፈት ነበር፡፡”ሲል የጉዳቱን አስከፊነት ይገልጸዋል፡፡

ተጫዋቹ ስፔኒያዊው ስፔሻሊሰት ሚሼል ሳንቼዝ ጋር በመሆን ይህን አስቸጋሪ ጊዜ ህክምናውን ሲከታተል የቆየ ሲሆን ሀኪሙም ተመሳሳይ አይነት ጉዳት ከዚህ ቀደም አጋጥሞት እንደማያቅ እንደገለጸ አሳውቋል፡፡

“እሱ የከፋ የኢንፌክሽን በሽታ እንዳጋጠመኝ ተረድቷል፡፡በሽታውም የአጥንቴን ክፍል እና የተረከዜን ጅማት ጎድቷቸው ነበር፡፡”ሲል ተናግራል፡፡

ካርዞላ ወደ ሜዳ ሊመለስ የሚችልበት ሁኔታ ካለ ተብሎ ከማርካ ለቀረበለት ጥያቄ ወደ ሜዳ በጥር ለመመለስ እቅድ መያዙን ጨምሮ አስረድቷል፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s