በቻምፕየንስ ሊጉ ባርሴሎናዎች አርሰናሎችን መግጠም ያስደስታቸው እንደነበር ዳኒ አልቬዝ ገለፀ

​የ34 አመቱ የቀድሞ የባርሴሎና ተጫዋች የነበረው ብራዚላዊው ዳኒ አልቬዝ ከካታላኑ ክለብ ጋር በነበረው ቆይታ በቻምፕየንስ ሊጉ ላይ አርሰናልን መግጠም ያዝናናቸው እንደነበር አሳውቋል።

ሁለቱ ቡድኖች በተደጋጋሚ በቻምፕየንስ ሊጉ የጥሎማለፍ ጨዋታ ላይ መገናኘት ቢችሉም አሸናፊ መሆን የቻሉት ባርሴሎናዎች ነበሩ።

2006 ላይ መድፈኞቹ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለ ትልቁን የቻምፕየንስ ሊግን ዋንጫን ለማንሳት የተቃረቡበት ወቅት ቢሆንም በፍጻሜው ከታሪካዊ ድላቸው ያደናቀፋቸው ባርሴሎና ነበር።

ባርሴሎና የስፔን እና የአውሮፓ እግርኳስን ተቆጣጥሮ በነበረበት በዚህ ወቅት ላይ አርሰን ዊንገር በአንድም ጊዜ ባርሴሎናን አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር መሸጋገር ሳይቻላቸው ቀርቷል።

በዚህም ምክኒያት ባርሴሎናዎች አርሰናልን መግጠም ያስደስታቸው እንደነበር የቀድሞ የክለቡ ተጫዋች የነበረው ዳኒ አልቬዝ አሳውቋል።

“ይጫወቱ የነበሩት ከኛ ጋር ተመሳሳይ አይነት እግርኳስ ነው።ይህም አንዳንድ ጊዜ በራሳችን መንገድ እንድንጫወት ያግዘን ነበር።

“ከነሱ ጋር ለብዙ ጊዜ አንድ ላይ ተመድበን ተጫውተናል።የነበረን ውጤትም ጥሩ ነበር።አርሰናል ማለት እኛ የበላይነት ወስደን የምናሸንፈው ቡድን ነበር።ሁልጊዜ እነሱን ስንገጥም ጥሩ ውጤት እናስመዘግብ ነበር።” በማለት አርሰናል ላይ የበላይነት በመውሰዳቸው እነሱን መግጠም ያስደስታቸው እንደነበር ሳኒ አልቬዝ ገልጿል።


Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s