የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር በኤቭራ ላይ የመጀመሪያ ያለውን የቅጣት ውሳኔ አሳለፈ

ፓትሪስ ኤቭራ ሃሙስ ምሽት ክለቡ ማርሴይ ከቪክቶሪያ ጊዩማራስ ጋር ዩሮፓ ሊግ ጨዋታ ከማድረጉ በፊት የገዛ ደጋፊውን መማታቱን ተከትሎ በአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የአንድ ጨዋታ የመጀመሪያ ያለውን የእገዳ ቅጣት ያስተላለፈበት ሲሆን፣ የድርጊቱን ሁኔታም መርምሮ ተጨማሪ የቅጣት ውሳኔ እንደሚያስተላልፍበትም ይጠበቃል።

የፈረንሳዩ ክለብ ማርሴ ፓትሪስ ኤቭራ ጨዋታው በፊት ከመጀመሩ በፊት የገዛ ክለቡን ደጋፊው በእግር በመራገጥ ለቀይ ካርድ የተዳረገበትን ምክኒያት ራሱ የውስጥ ምርመራ ማድረግ ጀምሯል።

ማርሴ በጨዋታው 1ለ0 ሽንፈት የደረሰበት ሲሆን፣ በአሰልጣኙ ሩዲ ጋርሺያ በተቀያሪዎች ዝርዝር ውስጥ ስሙ ተከቶ የነበረው ኤቭራም ክለቡ በዚህ ወር መጨረሻ ኮንያስፖርን በሚገጥምበት ጨዋታ ላይ ተሰልፎ የማይጫወት ይሆናል።

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር አርብ ባወጣው መግለጫ በማህበሩ የስነምግባር እና የስርኣት ቁጥጥር አካል አማካኝነት በሚቀጥለው ሳምንት ጉዳዩን ዳግም ተመልክቶ በተጫዋቹ ላይ ተጨማሪ የቅጣት ውሳኔ ሊያሳልፍ እደሚችልም ገልፅዋል።

በቪቶሪያ ሽንፈት የገጠመው ማርሴ በዩሮፓ ሊጉ ምድብ አይ ከሬድ ቡል ሳልዝበርግ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

የ36 ዓመቱ የመስመር ተከላካይ ኤቭራ በዚህ የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች ላይ ለማርሴ 10 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት የቻለ ሲሆን፣ ማርሴ በሊግ 1 ላይ እስከሁን ባደረጋቸው 11 ጨዋታዎች ላይ ደግሞ አራት ጨዋታዎችን ማደረግ ችሏል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s