የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፊፋን ጥያቄ ችላ ብሎ ጠቅላላ ጉባኤውን ለማካሄድ ወስኗል

በዚህ ወር መጨረሻ በአዲስ አበባ እንዲደረግ ቀነ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የመካሄዱ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል እየተባለ በስፋት ቢነገረም፡፡ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ዝግጅቴን አጠናቅቄ ጠቅላላ ጉባኤውን የሚደረግበትን ቀን እየተጠባበኩ እገኛለው ብሏል፡፡  ፊፋ በሳምንቱ መጨረሻ ላከው በተባለው ደብዳቤ መሰረት ከሆነ ግን ጠቅላላ ጉባኤው ላልተወሰኑ ቀናት ሊራዘም እንደሚችል በስፋት እየተነገረ ይገኛል፡፡

ፊፋ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጻፈው ደብዳቤ መሰረት ከአንድ ወር በፊት በምርጫው ላይ የሚሳተፉ የአስመራጭ የቦርድ  አባላት ስም ዝርዝር ስላልተላከልኝ በዚህ ወር መጨረሻ የሚደረገውን ምርጫ  ሰርዙልኝ ያለ ሲሆን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም በጉዳዩ ዙሪያ እስካሁን ለፊፋ ምላሽ አለመስጠቱ ተነግሯል፡፡

ሆኖም ከፌዴሬሽኑ ወጣ በተባለ መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስረኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጥቅምት 30 እና ህዳር 1 እንደሚካሄድ አሳውቋል፡፡ ሆኖም በጠቅላላ ጉባኤው ላይ የሚነሱ ጉዳዮች በሙሉ ግን ከምርጫው  በፊት በአጀንዳነት እንደሚነሱም  የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፊፋን ትህዛዝ በመጣስ ጠቅላላ ጉባኤውን ካገባደደ በኋላ የፕሬዝዳንታዊ እና የስራ አስፈጻሚዎች ምርጫ የሚያካሂድ ከሆነ ከአለም እግር ኳስ አስተዳዳሪው አካል ኮስተር ያለ ቅጣት የሚጠብቀው ሲሆን ምን አልባትም ሀገሪቷን እስከ  ሁለት አመታት ከማንኛውም ውድድር እስከማገድ ሊደርስ የሚችል ቅጣት ሊጣልበት ይችላል፡፡

 

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s