ድብድብ / የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ ባለስልጣናት ለጸብ ተጋበዙ

የምርጫ ዘመኑን ለማጠናቀቅ ቀናት የቀሩት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ እና ፕሬዝደንት በተለያዩ ጉዳዩች ዙሪያ ከሰሞኑ ከስምምነት መድረስ የተሳናቸው ሆነዋል፡፡ በተለይም በብሄራዊ ቡድኑ የቻን ተሳትፎ ዙሪያ ከፍተኛ ጭቅጭቅ ውስጥ መሰንበታቸው የተሰማ ሲሆን ዛሬ ከሰዓት በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ባደረጉት ሌላኛው ስብሰባ ደግሞ ለድብድብ የቀረበ ጸብ ውስጥ መግባታችው ተነግሯል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከፊፋ የደረሰውን ጥቅምት 30 ሊደረግ የታሰበው የፌዴሬሽኑ የፕሬዝዳንቲዊ እና የስራ አስፈጻሚ  ምርጫ ለጊዜው ይቆይ ጥያቄን ተከትሎ  ስብስበሳ ተቀምጦ የነበረው  የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ሰዓት ከፍተኛ ግጭት ውስጥ የገባ ሲሆን ፕሬዝደነት ጁነዲን ባሻ እና አቶ አበበ ገላጋይ ደግሞ ከተጋጩት ባለስልጣናት መካከል ዋነኞቹ እንደሆኑ ሀገሬ ስፖርት ዘግቧል፡፡

እንደ ሀገሬ ስፖርት ዘገባ ከሆነ ደግሞ አመራሮቹ የተጋጩት ምርጫው አይካሄድ እና ይካሄድ በሚሉ ጽንፍ ሀሳቦች ሲሆን በተለይም ፕሬዝደንቱ አቶ ጁነዲን ባሻ ምርጫው ላልተወሰነ ጊዜ ይተላለፍ ማለታቸውን ተከትሎ ከስራ አስፈጻሚው ኮሚቴ አባል ከሆኑት አቶ አበበ ገላጋይ ጠንካራ ትችት የተሰነዘረባቸው ሲሆን በውሳኔው የተበሳጬት አቶ አበበም ሀይላንድ እስከ መወርወር የደረሰ ቁጣቸውን የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ላይ መሰንዘራቸውን ሀገሬ ስፖርት አክሎ ገልጽዋል፡፡

ከምርጫው ቀደም ብሎ የፌዴሬሽኑ አመራሮች በጸብ ውስጥ ማለፋቸውን የተያያዙት ሲሆን ሌሎች አመራሮችም ከዚህ ቀደም በሀሳብ አለመስማማት ምክንያት እስከ መዘጋጋት የደረሰ ቁርሾ ውስጥ መግባታቸው ሲነገር ሰንብቷል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s