ፓትሪክ ኤቭራ ደጋፊን ደብድቦ ከዩሮፓ ሊግ ጨዋታው በፊት በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናበተ

1995 ኤሪክ ካንቶና በሴልሁርስት ፓርክ አንድ ደጋፊን በኩንግፉ የመታውን ያስታወሰ ድርጊት የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትዱ ፓትሪክ ኤቭራ ትናንት በዩሮፓ ሊግ ምሽት አንድ ደጋፊን በመምታቱ ጨዋታው ሳይጀመር በቀይ ካርድ ወጥቷል።

ማርሴ ወደ ፓርቹጋል አቅንቶ ከቪክቶሪያ ጉይሜሬስ ጋር ያደረገው የምሽቱ ጨዋታ ከጨዋታው ቀደም ብሎ ፓትሪክ ኤቭራ ከሜዳ በቀይ ካርድ የወጣበት ድርጊት የዛሬ የጋዜጦች ርእስ ሆኗል።

የቀድሞ የሞናኮ፣የማንችስተር ዩናይትድ እና የጁቬንቱስ የግራ እግር ተከላካይ ዘንድሮ በማርሴ ደጋፊዎች ተደጋጋሚ ትችቶች እየቀረበበት ይገኛል።

በምሽቱ ጨዋታ ላይም ስሙ በተጠባባቂ ተጫዋቾች ዝርዝር ውስጥ እንጂ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ያልተካተተው ኤቭራ ከጨዋታው ቀደም ብሎ ከቡድኑ ጋር ሲያሟሙቅ ታይቷል።

ነገርግን የማርሴ ደጋፊዎች ተቀምጠውበት ከነበሩበት አካባቢ ጠርዝ ላይ ከደጋፊዎች የቀረበበት ተቃውሞ እራሱን መቆጣጠር እንዳይችል አድርጎታል።

ኤቭራ ልምምዱን አቋርጦ የማስታወቂያው ቦርድ ጋር ተጠግቶ የነበረውን አንድ ደጋፊን ግራ እግሩን ከፍ አድርጎ ፊቱ ላይ አሳርፎታል።

ደጋፊው ለጥቃት የተዳረገው የዘረኝነት ስድብ በመሳደቡ እንደሆነ የተለያዩ መረጃዎች አመላክተዋል።

በተጠባባቂነት ስሙ ተመዝግቦ የነበረው ኤቭራ በሰራው ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ እንዲወጣ ተደርጓል።ጥፋቱም ጠንካራ በመሆኑ ከአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ተጨማሪ ቅጣት ይጠብቀዋል።

በዩሮፓ ሊግም ከጨዋታው መጀመር ቀደም ብሎ በቀይ ካርድ የወጣ የመጀመሪያ ተጫዋች እንደሆነ ታውቋል።

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s