ቅጣት / ኦሎምፒክ ዲ ማርሴ ፓትሪክ ኤቭራን አገደ

ፓትሪክ ኤቭራ ሀሙስ ምሽት የራሱን ክለቡ ደጋፊን እግሩን አንስቶ ከተማታ በኋላ ክለቡ ኦሎምፒክ ዲ ማርሴ በተጫዋቹ ላይ የእገዳ ውሳኔ ማሳለፉን አሳውቋል።

የዩሮፓ ሊግ ጨዋታን ለማድረግ ወደ ፖርቹጋል ያቀናው ኦሎምፒክ ዲ ማርሴ 1 ለ 0 ተሸንፎ ቢመለስም ከሽንፈቱ በበለጠ መነጋገሪያ የሆነው የፈረንሳዊው ፓትሪክ ኤቭራ ቀይ ካርድ ነበር።

የ 36 አመቱ ኤቭራ ወደ ፖርቹጋል አቅንተው ሊደግፏቸው ካቀኑት ደጋፊዎች ውስጥ ወደ ማስታወቂያው ቦርድ ጋር የተጠጋው አንዱን ደጋፊ በእግሩ በማታቱ ጨዋታው ሳይጀመር በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

1995 ኤሪክ ካንቶና የማንችስተር ዩናይትድን ማሊያ ለብሶ ሰልሁርስት ፓርክ ላይ ማቲው ሲሞንስ የተባለውን ደጋፊ በኩንጉፉ ከመታው ጋር የተመሳሰለው የፓትሪክ ኤቭራ ጥፋት ከክለቡም ይሁን ከአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ጠንከር ያለ ቅጣት እንደሚጠብቀው ይጠበቃል።

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበርም ጉዳዩን በጥልቀት መመርመር የጀመረ ሲሆን ለጊዜው ግን የመጀመሪያ የአንድ ጨዋታ ቅጣት ማሳለፉ ትናንት አሳውቋል።

ኤቭራ ትዕግስተኛ መሆን ይገባው እንደነበር ብዙዎቹ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል

ክለቡ ኦሎምፒክ ማርሴም እንዲሁ በክለቡ የስነምግባር ኮሚቴ ታይቶ ዛሬ ውሳኔ እስኪተላለፍበት ድረስ ከክለቡ ተጫዋቹን ማገዱን አሳውቋል።

የክለቡ ፕሬዝዳንት የሆኑት ጃኩዊስ ሄንሪ ኢራውድ አርብ ለታ ከተጫዋቹ ጋር በመገናኘት የስነምግባር እርምጃ ከመውሰዳቸው ቀደም ብለው ለቃለመጠይቅ እንደሚጠሩት እስከዛው ድረስ ግን ክለቡ እንዳገደው አሳውቀውታል።

ማርሴ ዛሬ በሚቀርበው የክለቡ የስነምግባር ኮሚቴ መረጃ መሰረት ከፓትሪክ ኤቭራ ጋር ያለውን ኮንትራት እንደሚቀድ የሚጠበቅ ሲሆን የአውሮፓ እግርኳስ ማህበርም በድጋሚ ህዳር 10 ላይ ከተወያየ በኋላ ጠንካራ ቅጣት እንደሚያሳልፍበት ይጠበቃል።

የቅጣት መጠኑም ምናልባትም ለ 36 አመቱ ተጫዋች የእግርኳስ ህይወቱ በዚሁ ሊያጠናቅቅ የሚችልበት አጋጣሚ እንዲያስብ ሊያደርገው ይችላል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s