ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ከ ባየር ሙኒክ| የጨዋታ ቅድመ ቅኝት

በሁለቱ የጀርመን ቡንዳስሊጋ ኃያላን ክለቦች መካከል የሚደረገው ታላቅና አጓጊ ጨዋታ ዛሬ (ቅዳሜ) ምሽት ላይ ይካሄዳል። ስለዚህ የሚጠበቅ ጨዋታ ሊያውቋቸው ይገባሉ ያልናቸውን መሰረታዊ ነጥቦች እንደሚከተለው አሰናድተንዎታል።

ምን ዓይነት ውድድር ነው?

ጨዋታው ባየር ሙኒክ ወደቦሩሲያ ዶርትሙንድ አቅንቶ የሚያደረገውና በዚህ የውድድር ዘመን በሁለቱ ክለቦች መካከል የሚደረግ የመጀመሪያ ጨዋታ ነው።

ጨዋታው መቼ ይደረጋል?

ይህ ጨዋታ ዌስትሃም ሊቨርፑልን በሚገጥምበት ተመሳሳይ ሰዓት ላይ የሚደረግ የቅዳሜ ምሽት ጨዋታ እንደመሆኑ ምርጫዎን ከወዲሁ ማስተካከል ይችላሉ። 

ጨዋታው ስንት ሰዓት ላይ ይደረጋል?

ጨዋታው በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠት ምሽት 2፡30 ላይ ይጀምራል።

ጨዋታው በየትኛው የቴሌቪዥን ቻናል ይተላለፋል?

በአውሮፓ ቢቲስፖርትስ 2 የዚህን ጨዋታ የቀጥታ ሽፋን ሰጥቶ ሲያስተላልፈው በአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች የዲኤስቲቪው ሱፐር ስፖርት እና በመከከለኛው ምስራቅና በሰሜን አፍሪካ ቢኢንስፖርትስ ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ሽፋን ይሰጡታል።

የቡድኖቹ ዜናዎች ምን ይመስላሉ?

የዶርትሙንዱ አሰልጣኝ ፒተር ቦሽዥ ከአፖል ኒኮሲያ ጋር ባደረጉት የረቡዕ ምሽቱ የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ጠንካራ ቡድናቸውን ቢያሰልፉም፣ በዚህም ጨዋታ በመጀመሪያው 11 ተሰላፊ ቡድናቸው ውስጥ ተመሳሳይ ተጫዋቾችን እንደሚያካትቱም ይጠበቃል። ኮከብ ተጫዋቹ ማርኮስ ሮይስ ከዚህ ቀደም በገጠመው ጉዳት ምክኒያት አሁንም ወደጨዋታ የማይመለስ ተጫዋች ነው። በሌላ በኩል የቀኝ መስመር ተከላካዩ ሉካዝ ፔዥሺክ፣ ሰባስቲያን ሮድ እና ኤሪክ ደርም እንዲሁ በዚህ ጨዋታ ላይ የመሰለፍ ዕድል የማይኖራቸው ተጫዋቾች ናቸው።

የፕ ሄንክስም ልምድ ያለውን ፈረንሳዊ የክንፍ ተጫዋች ከገጠመው የጉልበት ጉዳት ቢያገግምም በዚህ ጨዋታ ላይ ግን ማሰለፋቸው እርግጥ አይደለም። ግብ ጠባቂው ማኑኤል ኖየር በገጠመው የእግር ጉዳት አሁንም በማገገም ላይ የሚገኝ በመሆኑ ስቨን ኡልሪች ቦታውን ሸፍኖ የሚጫወት ይሆናል። እንዲሁም ሁለገብ ተጫዋቹ ኹዋን በርኔትም በዚህ ጨዋታ ላይ የማይሰለፍ ተጫዋች ነው። ከገጠመው የቋንጃ ጉዳት በማገገም ሃሙስ ዕለት የተሟላ ልምምድ መስራት የጀመረው ቶማስ ሙለር በሲግናል ኤዱና ፓርክ በሚደረገው በዚህ ጨዋታ ላይ ሊሰለፍ ይችላል።

እንዴት ዓይነት አሰላለፎች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃሉ?

ስለጨዋታው ምን ተባለ?

የዶርትሙንዱ አሰልጣኝ ቶማስ ቦሽዥ

በእርግጠኝነት አውቶቡስ ገትረን [ተከላክለን] ባየር ሙኒክን አንገጥምም።

ያ የእኛ የአጨዋወት ዘይቤ አይደለም። ማራኪ ጨዋታ ተጫውተህ ዋንጫዎችን ልታነሳ ትችላለህ። የእኔ ግብ ውብ በሆነ እግርኳስ ደጋፊያችንን ማስደሰት ነው። ያ ማለት ግን ዋንጫዎችን ያሳጣኸል ማለትም አይደለም።

ፔፕ ጋርዲዮላ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆን ይመስለኛል። እሱ ሁልጊዜም ማራኪ አጨዋወት ይጫወታል፤ ዋንጫም ያነሳል። ነገር ግን ቡድኖች አሁንም ድረስ በራቸውን ዘግተው ይጫወታሉ። ባየር እንዴት ይጫወት እንደነበር ስመለከት ይማርከኝ ነበር።

የባየር ሙኒኩ አሰልጣኝ የፕ ሄይንከስ፡ 

በመጀመሪያ ደረጃ ፒተር ቦሽዥ ጥሩ እግርኳስ ተጫዋች ነበር። እናም በአያክስ አሰልጣኝ ስትሆን ብዙ እውቀት ይዘህ መምጣት ይኖርብሃል። እሱም በእርግጠኝነት እውቀቱ አለው።

ሁሉም ሰው የራሱን ፍልስፍና ይዞ መምጣት የሚኖርበት ይመስለኛል። 

ዶርትሙንድ ይበልጥ ትኩረቱን ሰብስቦ ጥንቁቅ የሚሆን ይመስለኛል። ደጋፊዎቻቸውም ከባየር ሙኒክ ጋር ሲጫወቱ ይቅርታ ያዳረጉላቸዋል። እኛም ሲጫወቱ ተመልክተን በራሳችን አጨዋወት መንገድ ራሳችንን አዘጋጅተናል። ነገር ግን ይህን በሜዳ ላይ ማሳየት የሚጠበቅባቸው ተጫዋቾቹ ናቸው።

የሁለቱ ቡድኖች ቁጥራዊ መረጃዎች ምን ይመስላሉ?

  • ሁለቱ ቡድኖች ባደረጓቸው ያለፉት አራት ጨዋታዎች በርካታ ነጥቦችን መሰብሰብ የቻለው ባየር ሙኒክ ነበር።
  • ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ የውድድር ዘመን ብቻ ባየር ሙኒክ በ10ኛው ሳምንት ጨዋታ ወደቡንደስሊጋው አናት ከፍ ብሏል።
  • ሄይንክስ በመጀመሪያዎቹ የአስልጣኝነት ዘመኑ ሶስት ጨዋታዎች መረቡን ያላስደፈረ የመጀመሪያው የባየር ሙኒክ አሰልጣኝ ናቸው።
  • ሄይንክስ ከዶርትሙንድ ጋር ያዳርጉት የመጨረሻ ጨዋታ በ2012/13 በሻምፒዮንስ ሊግ ላይ ያደረጉት ጨዋታ ነበር። 
  • ሄይንክስ ባደረጓቸው ያለፉት የመጨረሻ 28 የቡንደስሊጋ ጨዋታዎች ሽንፈት ያልገጠማቸው ሲሆን፣ 24 ጨዋታ ሲያሸንፉ በቀሪ አራት ጨዋታዎች ደግሞ በአቻ ውጤት አጠናቀዋል። 
  • ባለፉት ስምንት ዓመታት ባየር ሙኒክ (ስምንት ጊዜ) እና ዶርትሙንድ (ሁለት ጊዜ) የቢንደስሊጋውን ዋንጫ በጋራ ማንሳት ችለዋል። ከ2009 አንስቶም ከ16 የቡንደስሊጋ እና የጀርመን ዋንጫዎች 14 ዋንጫዎችን ለሁለት ተቀራምተዋል።
  • ፒየር-ኤመሪክ አውባምያንግ እና ሮበርት ሊቫንዶውስኪ እያንዳንደቸው በ10 ግቦች የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነትን በጋራ እየመሩ ይገኛሉ። ሁለቱ አጥቂዎች በቡንደስሊጋው መጫወት ከጀመሩበት 2013 ጀምሮም በጋራ 202 ግቦችን ከመረብ ላይ ማሳረፍ ችለዋል። (ሊቫንዶውስኪ 107 እና አውባምየንግ 95)
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s