አስገራሚው የጨዋታ ውጤት ማጭበርበር በኮሞሮስ

በአፍሪካዊቷ ኮሞሮስ በሊጉ የመጨረሻ ጨዋታ ላይ የተፈጠረው የጨዋታ ማጭበርበር አስገራሚ ሆኗል።

ከእግርኳስ ጋር የተያያዙ የጨዋታ ውጤት ማጭበርበር አሁንም በአብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገራት ሊጠፋ ያልቻለ በሽታ ሆኖ ቀጥሏል።

በኛም ሀገር እንደዚሁ በየአመቱ የሊግ የመጨረሻ ጨዋታዎች ላይ አወዛጋቢ ክስተቶችን መመልከት አዲስ አይደለም።

የ2009 የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ የመጨረሻ ጨዋታም እንዲሁ በጅማ አባ ቡና፣በኢትዮ ኤሌትሪክ እና በሀዋሳ ከነማ ጋር በተያያዘ የጨዋታ ውጤት ማጭበርበር ክሶች በተደጋጋሚ ሲደመጡ እንደነበር አይረሳም።

አሁን ደግሞ ከወደ ኮሞሮስ አስገራሚ የጨዋታ ውጤት ማጭበርበር ዜና ተሰምቷል።በሊጉ የመጨረሻ ጨዋታ ላይ ሁለት ቡድኖች በእኩል 43 ነጥብ የደረጃው አናት ላይ ቢቀመጡም ዚሊማጁ የሚባለው ክለብ 19 ጎል ልዩነት በመያዝ ሲመራ ቮልካን ክለብ ደግሞ በ18 የጎል ልቱነት ተከትሎ የመጨረሻው ሳምንት ላይ ደርሰዋል።

በመጨረሻው ሳምንትም ሁለቱም ካሸነፉ የተሻለ የጎል ልዩነት ያለው የዋንጫ ባለቤት ይሆናል።

የተመዘገበው ውጤትም ይህን ይመስላል።

ዚሊማጁ 18-1 ጄኤሲ ኤም
ቮልካን ክለብ 21-0 ኤላን ክለብ
በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

ውጤቱ ተጋጣሚ ቡድኖች ሆን ብለው የጎል መጠኑ እንዲበዛ ያደረጉት በመሆኑ የሀገሪቷ የስፓርት ሚኒስቴር የእግርኳስ ፌዴሬሽን ሀላፊዎቹን ማገዱ ታውቋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s