የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከሩዋንዳ አቻው ጋር የቻን የማጣሪያ ጨዋታውን ያደርጋል

ኢትዮጵያ በሱዳን ሩዋንዳ በኡጋንዳ ተሽንፈው ያጡትን የቻን ተሳትፎ ለማግኘት ዳግም እድል ከካፍ  የተሰጣቸው ሁለቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት እሁድ ከሰዓት የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በአዲስ አበባ ስቴዲየም ያደርጋሉ፡፡ የሩዋንዳ ብሄራዊ ቡድን ለዚህ ጨዋታ በሳምንቱ መጨረሻ አዲስ አበባ የገባ ሲሆን ዋልያው ደግሞ ከቀናት በፊት ለዚህ ጨዋታ ማጣሪያ ልምምድ መጀመሩ ይታወቃል፡፡

በአሰልጣኝ አሸነፊ በቀለ የሚመራው ብሄራዊ ቡድኑ ለቻን አፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ ማጣሪያ ጨዋታ 27 ተጫዋቾችን ቢጠራም 23ቱ ብቻ በሆቴል ተገኝተው ልምምዳቸውን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ሰላዲን ሰይድ እና ጋዲሴ መብራቴ በጉዳት ምክንያት ከክለባቸው ፍቃድ ስላላገኙ ከብሄራዊ ቡድኑ ውጪ የሆኑ ሲሆን ዳዋ ሁጤሳ እና ሱራፌል ዳኛቸውም ከአዳማ ጋር ወደ ወልዲያ ማቅናታቸውን ተከትሎ ከመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ውጭ መሆናቸው እርግጥ ሆኗል፡፡

ትላንት አመሻሽ ወደ አዲስ አበባ የገባው የሩዋንዳ ብሄራዊ ቡድን በአንጻሩ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በተሻለ መልኩ ከካፍ ደብዳቤው እንደደረሰው ልምምዱን በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን በኪጋሊ የጀመረ ሲሆን ለጨዋታውም በሀገሪቱ አሉ የተባሉትን የሊጉን ተጫዋቾች መያዙ ተነግሯል፡፡

በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል መቀመጫቸውን ያደረጉት ሩዋንዳዎች ዛሬ በ10 ሰዓት ላይ ነገ ጨዋታቸውን በሚያደርጉበት አዲስ አበባ ስቴዲየም ልምምዳቸውን ይከውናሉ፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s