​​​ሮሜሉ ሉካኩ እየቀረበበት ላለው ትችት ምላሽ ሰጠ

የማንችስተር ዩናይትዱ አጥቂ ቤልጄማዊው ሮሜሉ ሉካኩ በሁሉም ውድድሮች ባለፉት ስድስት ጨዋታዎች ጎል ባለማስቆጠሩ ምክንያት እየቀረበበት ባለው ትችት ዙሪያ ምላሹን ሰጥቷል።

ከኤቨርተን 75 ሚሊየን ፓውንድ ወጥቶበት ቀያይ ሰይጣኖቹን የተቀላቀለው ሮሜሉ ሉካኩ ከቡድኑ ጋር በፍጥነት በመዋሀድ በመጀመሪያዎቹ 11 ጨዋታዎች 11 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

ነገርግን ለመጨረሻ ጊዜ ክሪስታል ፓላስ ላይ ካስቆጠረ በኋላ በሁሉም ውድድሮች ያደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች ላይ ጎል ማስቆጠር ተስኖታል።

በዚህም ምክንያት ከአንዳንድ ደጋፊዎች ተቃውሞ እየቀረበበት የሚገኝ በመሆኑ የቡድኑ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ ደጋፊዎች ድጋፍ ሊያደርጉለት እንደሚገባ መናገራቸው ይታወሳል።

ሉካኩ ከቀድሞ የአርሰናል ኮከብ ትየሪ ኦነሪ ጋር በነበረው ቃለ ምልልስ ላይ ትችቱን አስመልክቶ ምላሹን ሰጥቷል።

“አንዳንድ ሰዎች የጨዋታ ዘመኔን የጨርስኩ አድርገው የሚያስቡ አሉ። እኔ ገና 24 አመቴ በመሆኑ እንደጨረስኩኝ አድርጋችሁ ማሰብ አትችሉም። የመጨረሻ ብቃቴ ላይ ደርሼ አቋሜ እየወረደ የሚገኝበት ወቅት ሳይሆን የምሻሻልባቸው ቀሪ አመታቶች ከፊትለፊቴ አሉኝ

“ብዙ ችሎታዎች እንዳሉኝ አውቃለው።ጎሎችን በግራ፣በቀኝ እና በጭንቅላቴ ማስቆጠር እችላለው። ነገርግን ፈጣሪ መሆን እና ብዙ ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን ማቀበል እፈልጋለው። ቡድኔም በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ሲሆን እኔ እንዳለው እንዲያስቡ እፈልጋለው

“አሁን በጥሩ ጊዜ እና እድሜ ላይ እገኛለው። አሸናፊ ሆኜ የእግርኳስ ህይወቴን ወደ ቀጣዩ ምእራፍ ማሳደግ እፈልጋለው። “ሲል እየተሻሻለ የሚሄድበት እድል እንዳለው በማስረዳት ለትችቱ ምላሽ ሰጥቷል።

Advertisements
Posted in Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s