ማንችስተር ሲቲ ከ አርሰናል| የጨዋታ ቅድመ ቅኝት


አርሰናል ባለፈው የውድድር ዘመን የካቲት ወር በኤፍኤ ዋንጫ ጫዋታ ማንችስተር ሲቲን ድል ለማድረግ የቻለ የመጨረሻው ቡድን ሲሆን በዛሬው ጨዋታም በዚህ የውድድር ዘመን የመጀመሪያው ድል አድራጊ የፕሪሚየር ሊጉ ክለብ የመሆን ውጥን ይዞ ይህን ጨዋታ የሚያደርግ ይሆናል። በሌላ በኩል ሲቲ በፔፕ ጋርዲዮላ እየተመራ በሁሉም ውድድሮች ላይ ያስቆጠራቸውን ግቦች 49 ማድረሱ ለተጫዋቾቹ የአዕምሮ ጥንካሬ ስንቅ ይሆናቸዋል። አርሰናል ከሲቲ በዘጠኝ ነጥቦች ወዳትች ርቆ በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ በመቀመጡ ምክኒያት የዋንጫ ተፎካካሪነቱን ተስፋ ለማለምለም ሲል የግድ ይህን ጨዋታ ማሸነፍ ይጠበቅበታል። 

የጨዋታ ሰዓት፡ እሁድ 11፡15

ሜዳ፡ ኢትሃድ ስታዲየም

ባለፈው የውድድር ዘመን፡ ማን ሲቲ 2 አርሰናል 1

ቀጥታ ስርጭት፡ ስካይ ስፖርት ፕሪሚየር ሊግ (በእንግሊዝ)፣ ሱፐር ስፖርት 3 (ከሰሃራ በታች)፣ ቢኢን ስፖርት 11 (በሰሜን አፍሪከና መካከለኛው ምስራቅ)

የጨዋታው ዳኛ፡ ማይክል ኦሊቨር

ዳኛው በዚህ የውድድር ዘመን፡  አጫወቱ9፣ ቢጫ35፣ ቀይ2፣ 4.11 ካርድ በየጨዋታው

ግምታዊ አሰላለፎች

ማንችስተር ሲቲ

ተቀያሪዎች፡ ብራቮ፣ ማንጋላ፣ ቱሬ፣ አዳራቢዮ፣ ዲያዝ፣ ዳ. ሲልቫ፣  ሲልቫ፣ ኼሱስ፣ ዳኒሎ

መሰለፋቸው የሚያጠራጥር፡ የሉም

ጉዳት ያለባቸው፡ ሜንዲ (የጉልበት)፣ ኮምፓኒ (የባት)

ቅጣት ላይ የሚገኙ፡ የሉም

ወቅታዊ ውጤቶች፡ ድል፣ድል፣ድል፣ድል፣ድል

ካርዶች፡ ቢጫ19፣ ቀይ2

ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች፡ አጉዌሮ፣ ስተርሊንግ 7

አርሰናል

ተቀያሪዎች፡  ማሲ፣ ሊየቭ፣ ደቡቺ፣ ሆልዲንግ፣ ማይትላንድ-ኒለስ፣ ኮክሊን፣ ኤልኒኒ፣ ዊልሼር፣ ዋልኮታ፣ ኢዎቢ፣ ኔልሰን፣ ዥሩ፣ አክፖም 

ጉዳት ያለባቸው፡  ሙስታፊ (የቋንጃ)፣ ዌልቤክ (የብሽሽት)፣ ካዛሮላ (ከተረከዝ በላይ ያለ የእርግ ክፍል)

 መሰለፋቸው የሚያጠራጥር፡ ቻምበርስ፣ ኮላሲናች (ሁለቱምበዳሌ ጉዳት)፣ ኦስፒና (የብሽሽት)

ቅጣት ያለባሸው፡ የሉም

ወቅታዊ ውጤቶች፡ አቻ፣ ድል፣ ድል፣ ሽን፣ ድል፣ ድል

ካርድ፡ ቢጫ9 ቀይ0

ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ፡ ላካዜቲ 5

አሰልጣኞቹ ምን አሉ?

የማንችስተር ሲቲው ፔፕ ጋርዲዮላ፡ ስለአርሰናል ያለሽንፈት ጉዞ ያደረጉበት 2003-04 የውድድር ዘመን “አርሰን ቬንገርን ያ ክብረወሰን የራሱ ነው። ያን እኛ አንሰብረውም። ዘና ማለት ይኖርበታል።

“ልዩ ቡድን ነበር። በፕሪሚየር ሊጉ ላይ አለመሸነፍ የሚያስደንቅ ነገር ነው። እኛም ልንሰብረው አንፈልግም። ነገር ግን ባእሁድ ዕለቱ ጫዋታ ግን ጥሩ መጫወትና እነሱን ማሸነፍ እንፈልጋለን።”

የአርሰናሉ አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር፡ ” ይህ ጨዋታ እንዲህ ዓይነት ጨዋታዎችን እንዴት መወጣት እንደምንችል ማሳየት የምንችልበት ዕድል ነው። እናም ያን ማድረግ እንደምንችል እርግጠኛ ነኝ።

“በአሁኑ ጊዜ ጠንከር ብለን በአግባቡ ራሳችንን ማዘጋጀትና ለእሁዱ ጨዋታ ከፍተኛ ትኩረት መስጠት አለብን።

“በ[በጨዋታው ላይ] አንደበቅም። አንዳድን ጊዜ ለመከላከል የተሻለው መንገድ ማጥቃት ነው።”

የጨዋታው እውናታዎች

በእርስ በርስ ግንኙነት

  • ማንችስተር ሲቲ በዘጠኝ ጨዋታዎች አርሰናልን ማሸነፍ የቻለው ባለፈው የውድድር ዘመን በሊጉ በኢትሃድ 1ለ0 ማሸነፍ የቻለበት ጨዋታ ነው።
  • አርሰናል ባደረጋቸው 10 ጨዋታዎች በስምንቱ ላይ በትንሹ ሁለት ግቦችን ከመረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል። በተመሳሳይ ጨዋታዎች ላይ ደግሞ ሲቲ መረቡን ሳያደፍር መውጣት አልቻለም
  • ሲቲ በአርሰናል 24ኛው ሽንፈት የሚደርስበት ከሆነ በፕሪሚየር ሊጉ በቼልሲ ከደረሰበት ከፍተኛ ሽንፈት ጋር ይስተካከላል።
    Advertisements