ቼልሲ ከ ማንችስተር ዩናይትድ| የጨዋታ ቅድመ ቅኝት

ጆዜ ሞሪንሆ በሳምንቱ መጨረሻ በሻምፒዮንስ ሊጉ በሮማ ሽንፈት የደረሰበትን የአንቶኒዮ ኮንቴን በድን ለመግጠም ዳግም ወደስታንፎርድ ብሪጅ ይመለሳሉ። አንቶኒዮ ኮንቴም ከገጠማቸው የሽንፈት ድባብ ውስጥ የመወጣት ዕቅድ ይዘው ማንችስተር ዩናይትድን በስታንፎርድ ብሪጅ ያስተናግዳሉ። 

የጨዋታ ሰዓት፡ ምሽት 1፡30 

ሜዳ፡ ስታንፎርድ ብሪጅ

ባለፈው የውድድር ዘመን፡ ቼልሲ 4 ማን ዩናይትድ 0

የቀጥታ ስርጭትስካይ ስፖርት ፕሪሚየር ሊግ (በእንግሊዝ)፣ ሱፐር ስፖርት 3 (ከሰሃራ በታች በአፍሪካ) እና ቢኢንስፖርት 11 (በሰሜን አፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ)

የጨዋታው ዳኛ፡ አንቶኒ ቴይለር

ዳኛው በዚህ የውድድር ዘመን፡ አጫወቱ6፣ ቢጫ23፣ ቀይ0፣ 3.83 ካርዶች በየጨዋታው።

ግምታዊ አሰላለፎች

ቼልሲ
ተቀያሪዎች፡ ካባሌሮ፣ ኤድዋርዶ፣ ስኮት፣ ክርስቲያንሰን፣ ክላርክ-ሳልተር፣ ሙሶንዳ፣ ኬኔዲ፣ ፋብሪጋዝ፣ አምፓዱ፣ ባካዮኮ፣ ስተርሊንግ፣ ባቱሹአዪ፣ ዊሊያን

መሰለፋቸው የሚያጠራጥር፡  ባካዮኮ (የብሽሽት)፣ ሃዛርድ (የተረከዝ)፣ ካንቴ  (የቋንጃ)፣ ሞራታ (በሙሉ አቋም ላይ ያለመገኘት)

ጉዳት ያለባቸው፡ ሞሰስ (የቋንጃ)

በቅጣት ላይ ያሉ፡  የሉም

ወቅታዊ ውጤት፡ ድል፣ አቻ፣ አቻ፣ድል፣ድል

ካርዶችቢጫ15 ቀይ3

ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ፡ ሞራታ 6

ማንችስተር ዩናይትድ

ተቀያሪዎች፡ ፔሬራ፣ ሮሜሮ፣ ሻው፣ ቱኣንዜቤ፣ ሊንዶልፍ፣ ማርሺያል፣ ማክቲሞኒ፣ ሚቼል፣ ዳርሜን፣ ብሊንድ

መሰለፋቸው የሚያጠራጥር፡ ሊንጋርድና ሮኾ፣ (ሁለቱም በሙሉ ብቃት ላይ ያለመገኘት)

በጉዳት ላይ የሚገኙ፡ ፖግባ፣ (የቋንጃ)፣ ኢብራሂሞቪች (የጉልበት)፣ ካሪክ (የባት) 

በቅጣት ላይ የሚገኙ፡  የሉም

ወቅታዊ ውጤቶች፡  ድል፣ድል፣ድል፣ሽን፣ድል

ካርዶችቢጫ14 ቀይ0

ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ፡ ሉካኩ 7

አሰልጣኞቹ ስለጨዋታው ምን አሉ?

የቼልሲው አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ፡ “አሁን ዋንጫውን ለማንስሣት በመፈለጉ በኩል በሁሉም ቡድኖች ላይ ትልልቅ ችግሮች አሉ።  ትልቁ ችግርም ማንችስተር ሲቲ ነው።

“ሲቲ በዚህ መንገድ የሚቀጥል ከሆነ ለዋንጫ የሚደረገውን ፉክክር አስቸጋሪ ያደረገዋል። እኛም የምንችለውን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅብናል።”

የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሆዜ ሞሪንሆ ከቀድሞ ክለባቸው ቼልሲ ጋር ስለመጫወታቸው ጉዳይ የተናገሩት፡ “የተወሰነ ልዩነት እንዳለው ማመን ይኖርብኛል። ነገር ግን በኢንተር እንዳደረክጉት ሁሉ በመጨረሻ ማሸነፍ እፈልጋለሁ። እነሱም ባለፈው የውድድር ዘመን እንዳደረጉት ሁሉ ማሸነፍ ይፈልጋሉ። ገና አንድ ቀሪ ቀን ግን አለን። 

“በተወሰኑ ዓመታት ውስጥ ይበልጥ የቀድሞ ብቃታችንን እናመጣለን። ከአራትና አምስት ዓመታት በኋላ ማንም ሰው የቼልሲ አሰልጣኝ እንደነበርኩ አያስታውስም እናም ሁሉም ነገር ጤናማ ይሆናል።

“ይህ ትልቅ ነገር አይደለም። አንድ ቀን በአንድ ክለብ ውስጥ ትገኛለህ። ሌላ ጊዜ ዳግሞ በሌላ።” 

የጨዋታው እውነታዎች

የሁለቱ ቡድኖች እርስበርስ ግንኙነት

  • ቼልሲ ከዚህ ቀደም ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ባደረጋቸው 15 የስታንፎድ ብሪጅ ጨዋታ ሽንፈት የገጠመው በአንዱ ብቻ ነው። (ድል 9፣ አቻ5)
  • ዩናይትድ በየካቲት ወር በሊጉ ያደረገው ድል (2ለ0) የቼልሲን በሁሉም ውድድሮች ላይ የ12 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞን መግታት የቻለ ነበር።
  • ቀያይ ሰይጣኖቹ በፕሪሚየር ሊጉ በቼልሲ ከደረሰባቸው ሽንፈት (17) እና ከተቆጠረባቸው ብዙ ግቦች (66) በላይ ያሸነፋቸው እና ያስቆጠረባቸው የፕሪሚየር ሊግ ክለብ የለም።
Advertisements