የማንችስተር ዩናይትዱ አጥቂ ዝላታን ኢብራሂሞቪች ከዋናው ቡድን ጋር ልምምድ ጀመረ

Image result for Zlatan Ibrahimovic

ከወራት የማገገም ሂደት በኋላ ስዊዲናዊው አጥቂ ዝላታን ኢብራሂሞቪች ከማንችስተር ዩናይትድ ዋናው ቡድን ጋር ልምምድ ጀምሯል፡፡ ቀያዮቹ ሰይጣኖች ባሳለፍነው አመት በኦሮፓ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ዩናይትድ ከአንደርሌክት ጋር ባደረገው ጨዋታ  ላይ ከባድ የተባለ የጉልበት ጉዳት የገጠመው ስዊዲናዊው በመጨረሻም ከጉዳቱ ሙሉ ለሙሉ አገግሞ ልምምድ መጀመሩን ስካይ ስፖርት ዘግቧል፡፡

እንዴት አንበሳን ከሰው ጋር ታነጻጽራላቹ በማለት ራሱን በአንበሳ የመሰለው ግዙፉ አጥቂ በካሪንግተን የልምምድ መሀከል ከቡድን ጓደኞቹ ጋር በመሆን ልምምዱን ሲከውን የታየ ሲሆን ጠንካራ ሹቶችን ወደ ግብ ጠባቂዎች በመምታትም ራሱን በሚገባ እያዘጋጀ እንደሆነ አሳይቷል፡፡

ከጉዳት መልስ በቀጣዩ ወር መጨረሻ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ የሚጠበቀው ዝላታን ኢብራሂሞቪች  በማንችስተር ዩናይትድ  ቤት በውድድር ዘመኑ ጅማሮ በአስራ ስድስት ጨዋታዎች  አስራ አንድ ግቦችን ማስቆር ከቻለው ሮሜሉ ሉካኮ ከባድ ፉክክር ይጠብቀዋል፡፡ ሆኖም ግን  ቤልጄማዊው የቀድሞ የኤቨርተን አጥቂ በተከታታይ ስድስት ጨዋታዎች ላይ ግቦችን አለማስቆጠሩን ተከትሎ ከወዲሁ  ከዩናይትድ ደጋፊዎች ትችት እየደረሰበት ይገኛል፡፡

የቀድሞውን የማንችስተር ዩናይትድ አምበል መለያ የሆነውን አስር ቁጥርን የተከረከበው 36 አመቱ አጥቂ ባሳለፍነው የውድድር ዘመን የጆዜ ሞሪንሆ ተቀዳሚ የፊት ምርጫ የነበረ ሲሆን በውድድር ዘመኑም በ46 ጨዋታዎች 28 ግቦችን በሁሉም ውድድሮች በማስቆጠር የክለቡ ከፍተኛ ግብ አግቢ በመሆን ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

Advertisements