ሹመት/ዌስትሀም ዩናይትድ ዴቪድ ሞይስን አሰልጣኙ አድርጎ ሾመ

West Ham will confirm David Moyes as their new manager on Tuesday

ዛሬ ረፋድ ክሮሺያዊውን አሰልጣኝ ስላቫን ቢልችን የሸኘው ዌስትሀም ዩናይትድ ነገ በይፋ የቀድሞውን የማንችስተር ዩናይትድ ኤቨርተን እና ሰንደርላንድ አሰልጣኝ የነበሩትን ስኮትላንዳዊውን ዲቪድ ሞይስ እንደሚሾም ተረጋግጧል፡

ባሳለፍነው አመት ከጥቋቁር ድመቶቹ ሰንደርላንዶች ጋር ያልተሳካ የውድድር ዘመን ማሳለፍ የቻሉት ስኮትላንዳዊው ነገ በይፋ አዲሱ የዌስትሀም አሰልጣኝ ሆነው እንደሚሾሙ ታማኙ ስካይ ስፖርት የክለቡ ምንጮቼ ሹክ አሉኝ በማለት ዘግቧል፡፡

ዲቪድ ሞይስ ለንደኑ ክለብ የስድስት ወራት ኮንትራት የሚፈራረሙ ሲሆን በውድድር አመቱም ዌስትሀም ዩናይትድን ከገባበት የውጤት አዘቅት የማውጣት ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡

በዘንድሮ የውድድር ዘመን በሊጉ ግርጌ ላይ 18ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ዌስትሀም ዩናይትድ ዴቪድ ሞይስ በታሪክ 16ኛው የክለቡ አሰልጣኝ ናቸው፡፡ ስኮትላንዳዊው አለቃ የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታቸውን ኖቬምበር 19 በቪካሬጅ ሮድ ዋትፎርድን በመግጠም ይጀምራሉ፡፡

 

Advertisements