እጩ/ አልማዝ አያና የአለም ምርጥ ሴት አትሌት የመጨረሻዎቹ ሶስት እጩዎች ውስጥ ተካተተች

Image may contain: 6 people, people smiling, text

አንጸባራቂ አመት በግሏ ማሳለፍ የቻለችው አትሌት አልማዝ አያና ለአለም  ምርጥ ሴት አትሌት የመጨረሻዎቹ ሶስት እጩዎች ውስጥ  ተካታለች፡፡ አትሌቷ ባሳለፍነው አመት በለንደን በተካሄደው የአለም ሻምፒዮና ውድድር በ10 ሺ ሜትር ላይ የወርቅ ሜዳልያ ያስመዘገበች ሲሆን በ5 ሺ ሜትር ውድድር ደግሞ የብር ሜዳልያ በማግኘት ለግሏ እና ለሀገሯ አኩሪ ድል ማስመዝገብ ችላለች፡፡

ከወርሀ መስከረም አጋማሽ ጀምሮ በተካሄደው በዘንድሮ የአለም አትሌቲክስ የወንዶች እና የሴቶች ምርጥ አትሌቶች ምርጫ ውድድር ላይ በተለያዩ መንገዶች ምርጫው የተካሄደ ሲሆን የመጀመሪያው በIAAF  ካውንስል አባላት በሆኑ የአትሌቲክስ ሰዎች እንዲሁም በሶሻል ሚዲያ ላይ ደጋፊዎች በሚሰጡት ድምጽ በመመርኮዝ እስከ ኦክቶበር 16 ድረስ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት አብላጫ ድምጽ በወንድም በሴትም ማግኘት የቻሉት 6 አትሌቶች ይፋ የሆኑ ሲሆኑ በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አልማዝ አያና ግሪካዊቷ ኢካትሪኒ ስቴፋንዲ እንዲሁም የቤልጂሟ ናፊሳቱ ቲሃም የመጨረሻ 3 እንስት እጩዎች ሆነዋል፡፡ በወንዶች የታላቋ ብሪታኒያው ሞሆ ፋራህ የኳታሩ ሙታዝ ኢሳ ባርሺም እንዲሁም ዋይድ ቫን ኒይክረክ  ምርጥ ሶስት ውስጥ መካተት የቻሉ አትሌቶች ናቸው፡፡

የአመቱ የIAAF ምርጥ ሴትና ወንድ አትሌቶች የሽልማት ስነ ስርዓት በፈረንሳይ ሞናኮ እ.ኤ.አ ህዳር 24 እንደሚካሄድ IAAF ይፋ አድርጓል፡፡

Advertisements