የኢትዮጵያ ቮሊቮል ፌዴሬሽን ቮሊቮልን በመላ ሀገሪቱ ለማስፋፋት እና ለማሳደግ መወጠኑን አሳወቀ

Image may contain: 1 person, standing

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በራስ ሆቴል ስብስባውን ያደረገው የኢትዮጵያ ቮሊቮል ፌዴሬሽን ውድድሩን በመላ ሀገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ መወጠኑን አሳውቋል፡፡ በ2009 የተከወኑ ስራዎችን የገመገመው ፌዴሬሽኑ የበጀት አመቱን አፈጻጸም ላይ ውይይት ያደረገ ሲሆን የ2010 በጀት አመት እቅድንም ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት ቮሊቮል ከሌሎች ስፖርቶች አንጻር ሲታይ ዉጤታማ ባለመሆኑ ስፖርቱን በመላ ሀገሪቱ ለማስፋፋትና ለማሳደግ እንዲሁም በህብረተሰቡ ዘንድ ተዘዉታሪና ተፈቃሪ እንዲሆን የባለድርሻ አካላትና የስፖርት ቤተሰቡ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠዉ እንደሚገባ  የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ መስፍን አበራ ለተሰብሳቢዎች ተናግረዋል፡፡

በእለቱም  የበጀት አመቱን በቀረበውየእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አስመልክቶም ከተሳታፊዎች  እና ከባለድርሻ አካላት  የዉድድር መድረኮች አለመዘጋጀት ፤ የስፖርታዊ ጨዋነት መጓድል፤ የፋይናስ እጥረት ፤ የአመራር መቀያየር ፤ የሚድያ ሽፋን እና ብሄራዊ ቡድን አለመኖር የመሳሰሉ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተንፀባርቀዉ በሚመለከተዉ አካል ምላሽ ተሰጥቷል ፡፡

11 ክለቦች በ2ቱመ ጾታዎች ተሳታፊ የነበሩበት የ2009   የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ  ውድድር በድምሩ 129 ስፖርተኞች ተሳታፊዎች እንደነበሩ ፌዴሬሽኑ በሪፖርቱ አሳውቋል፡፡ የ ቮሊቮል ፌዴሬሽን በእለቱ ሌላ ይፋ ያደረገው አጠቃለይ በአመት ውጥ 498.530 ብር ለሊጉ ተሳታፊ ክለቦች በሽልማት መልክ  ወጪ ማድረጉን በሪፖርቱ ገልፅዋል፡፡

Advertisements