የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ

23130846_604011906435714_3908904865317592144_n

የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል አካሂዷል፡፡

በእለቱም የጠቅላላ ጉባኤው አባላት እና እና ባለድርሻ አካላት በስብሰባው የታደሙ ሲሆን በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ አበባ አማረ አማካኝኘትንም የ2010 በጀት አመት እቅድ ይፋ ሆኗል፡፡ ከእቅዱ መውጣት በፊትም የ2009 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ ቃላ ጉባኤ ላይ መወያየትና ማፅደቅ የተካሄደ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ፌዴሬሽኑ እና በክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች በኩል በ2009 ዓ.ም የተሰሩት ስራዎች ላይ ውይይት አድርጓል፡፡

ሌላው በጠቅላላ ጉባኤው በክለቦች አደረጃጀት ዙሪያ በፌደሬሽኑ የተሠራ ጥናታዊ ፅሑፍ  የቀረበ ሲሆን ተሳታፊዎችም በጽሀፉ ዙሪያ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡ በተያያዘ ሁሉም አጀንዳዎች ላይ የጉባኤው ተሳታፊዎች ሰፋ የለ ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ በሙሉ ድምፅ ጸድቋል፡፡
የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ  ፌዴሬሽን  በ2010 ዓ.ም የተሻለ ስራ ለመስራት ማቀዱን በእለቱ ይፋ ያደረገ ሲሆን በተለይ የህብረተሰቡን በወድድር ፣በባለሙያ ስልጠና ፣ በውጭ ግንኝነት እና በተለያዩ ኩነቶች ተሳታፊ እና ተጠቃሚ ለማድረግ መወጠኑን ይፋ አድርጓል፡፡

Advertisements