ሞሪንሆ በዩናይትድ ፔፕ ጓርዲዮላ በሲቲ ያገኘውን ያህል ነጻነት እንዳላገኘ ማርሴ ዴሳይሊ ገለፀ

የቀድሞ የቼልሲ ተከላካይ የነበረው ፈረንሳዊው ማርሴ ዴሳይሊ ጆሴ ሞሪንሆ ማንቸስተር ዩናይትድን በራሳቸው ፍልስፍና መልክ እስኪያስይዙት ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው በመናገር በቡድኑ ውስጥም ፔፕ ጓርዲዮላ በሲቲ ያለውን ያህል ነጻነት እንዳላገኙ ጨምሮ አሳውቋል፡፡

ማንቸስተር ሲቲ በአስገራሚ ብቃት ፕሪምርሊጉን መምራቱን ተከትሎ ከየአቅጣጫው ለፔፕ ጓርዲዮላ ቡድን ሙገሳ እየቀረበለት ይገኛል፡፡በተለይም ቡድኑ ብዛት ያላቸውን አዳዲስ ተጫዋቾችን አሰባስቦ ከቡድኑ ጋር የሚዋሀዱበት ጊዜ እንደሚያስገልጋቸው በሚጠበቅበት ወቅት በአንድ ጊዜ ቡድኑ ባማረ እንቅስቃሴ የዋንጫ ተፎካካሪዎቹን እያሸነፈ መቀጠሉ ለሙገሳው ዋናው ምክንያት ሆኗል፡፡

በተቃራኒው ደግሞ ለጆሴ ሞሪንሆው ዩናይትድ ትችቶች መቅረባቸው አላቆሙም፡፡በተለይ ቡድኑ ከሊቨርፑል ጨዋታ በኋላ እያሳየ ያለው እንቅስቃሴ ውጤት እያስገኘት አይገኝም፡፡ከትላልቅ ቡድኖች ጋርም ሲጫወት ቡድኑ በራሱ ሜዳ ላይ ብዙ ጊዜ እየቆየ ጥንቃቄ እና መከላከልን መሰረት ያደረገ ጨዋታን መምረጡ ለትችቱ ምክንያት ሆኗል፡፡

እንደ ቀድሞ የቼልሲው ተከላካይ ማርሴ ዴሳይ እምንት ግን ጆሴ ሞሪንሆ በማንቸስተር ዩናይትድ ፔፕ በሲቲ ያገኘውን ያህል ነጻነት አለማግኘቱን ይገልጻል፡፡“እሱ የቡድኑን አቅም ያውቃል፡፡ፔፕ ጓርዲዮላ የሚፈልጋቸው ተጫዋቾችን ማውጣት እና ማስገባት እንደቻለው ሁሉ ጆሴ ሞሪንሆ እንደ እሱ በዩናይትድ ቤት ነጻነት አላገኘም፡፡

“እስካሁን ድረስ በሱ ፍልስፍና የማይሄዱ ተጫዋቾችን እያስተካከለ ይገኛል፡፡አሁን እየሰራ የሚገኘው ጥሩ ነገር ነው፡፡ስለዚህ ቡድኑ በሰር አሌክስ ፈርጉሰን እንዳንጸባረቀው ሁሉ ወደ ቦታው እንደሚመልሰው ተስፋ አደርጋለው፡፡ነገርግን ሁሉ ነገር ጠንካራ ነው፡፡አሰልጣኙ እና ተጨዋቾቹ ትልቅ ታሪክ ተሸክመዋል ስለዚህ ለጆሴ ሞሪንሆ ጊዜ ሊሰጠው ያስፈልጋል፡፡” በማለት ድጋፉን ሰጥቷል፡፡

Advertisements