የሩሲያው የ2018 ዓለም ዋንጫ ተሳታፊ ሃገራት አዳዲስ መለያዎች 

በሩሲያ አዘጋጅነት የፊታችን ሰኔ ወር በሚካሄደው የ2018 የዓለም ዋንጫ በአሁኑ ጊዜ ከ32 ተሰታፊ የዓለም ሃገራት 23 ቡድኖች ተለይተው ታውቀዋል። 

የስምንት ወራት ጊዜ በቀሩት ታላቅ የዓለማችን ውድድር ተሳታፊ ከሚሁኑ ሃገራት ቡድኖች መካከል የበርካታዎቹ ሃገራት መለያዎች ይፋዊም ሆነ ይፋዊ ባልሆኑ መንገዶች ለእግርኳስ አፍቃሪው ተዋውቀዋል።

ሰላሳሁለቱ ሃገራት አብዝኛውን መለያዎችን የመስራት ከፍተኛ ድርሻ ያለው አዲዳስ የዋናዋናዎቹን ሃገራት መለያዎች ዲዛይን ይፋዊ በሆነ መልኩ ሰኞ ዕለት አስተዋውቋል። ሌሎቹ አበይት የትጥቅ አምራች ኩባንያዎቹም በፀደይ ወቅት የመረቷቸውን የመልያ ዲዛይኖች ይፋ ያደርጋሉ ተብለው ይጠበቃሉ። 

የትጥቅ አምራች ኩባንያዎች በሃያ ሶስቱ ሃገራት የመለያ ምርት ላይ ያላቸው ድርሻ

ኢትዮአዲስ ስፖርትም ተሳታፊ ሃገራቱ ከሚለብሷቸው የመጀመሪያ መለያዎች የአብዛኛዎቹን በይፋ የተለቀቁትን እና ይፋዊ ባልሆነ መልኩ አፈትልከው የወጡ የዓለም ዋንጫው ተሳታፊ ሃገራት መለያዎች ምን እንደሚመስሉ እንደሚከተለው ታስቃኝዎታለች።

ቤልጂየም

በጀርመኑ የስፖርት ትጥቅ አምራቹ አዲዳስ የተሰራው የቤልጂየም ማለያ ከ1984 የዓለም ዋንጫ ተሳታፊው ቡድኗ ጋር የሚመሳሰል ተደርጎ እንዲህ ዲዛይን በመሆን በይፋ ተዋውቋል።

ባትሹአዪ በአዲሱ ቤልጂየም መለያ

እንግሊዝ

በአሜሪካኑ የስፖርት ትጥቅ አምራች ናይክ የተሰረው የ2018 የዓለም ዋንጫ የእንግሊዝ መለያ በይፋ ባይተዋወቅም ነገር ግን  በፊት ለፊት ደረት ላይ ከሰማያዊና ቀይ የንድፍ ቅንጅት የተፈጠረ አብዛኛው ነጭ ቀለም ያለው ሆኖ የተጋዘጋጀ ነው። 

ከከዚህ ቀደሙ ለየት ባለ መልኩ የቀረበው የእንግሊዝ መለያ

ፈረንሳይ

በናይክ የተመረተው የፈረንሳይ የ2018 የዓለም ዋንጫ መለያ የተወሰኑ አዳዲስ ቀለማት ቢካተቱበትም እንዲሁም ሙሉ ገፅታው ምን እንደሚመስል ባይታወቅም  ከ2012 እና 2014 መለያ ጋር ግን ተመሳሳይነት ያለው ይመስላል። 

ጀርመን

የዓለም ዋንጫ ወቅታዊ አሸናፊዋ ጀርመን በአዲስ አምራችነት ያስተዋወቀችው መለያ የቀድሞውን ዘመን አይሽሬ መለያዋን መሰረት ባደረገ መልኩ አሰርታዋለች። በ2018 የዓለም ዋንጫ ላይ ለብሳ የምትጫወትበት መለያም አይረሴውን የ1990 የጀርመን ቡድንን የደረት ላይ ንድፍ አቀራረብ ተመሳስሎ ነገር ግን የቀለም ለውጥ ብቻ አድርጎ የተዘጋጀ ነው።

የ1990 ብሄራዊ ቡድኗን ተመሳስሎ የተዘጋጀው ነው

ጣሊያን

የፑሜ ምርት የሆነው የጣሊያን መለያ ደረቱ እና ከእጆቹ ስር ካሉ ነጣ ያሉ ንድፎች እና እጅጌ ጫፍና አንገትጌው ላይ ካሉ ጥቁር ቀለማት ውጪ ከበዛ የንድፍ ስራዎች የፀዳና ነፃ ዘመናዊ አሰራርን የተከተለ ሙሉ ሰማያዊ መለያ ነው።

በይፋ የለተዋወቀው የጣሊያን መለያ

ፖርቱጋል

አሁንም በድጋሚ የዚህች ሃገር የመለያ ምርት ባለቤት ናይክ ነው። የፖርቱጋል የ2018 የዓለም ዋንጫ መለያ በአይነቱ አዲስ የሆነ ንድፍንና አቀራረብ ያለውም ነው።

በዓይነቱ ለየት ያለው የጣሊያን መለያ

ሩሲያ

የ2018 ዓለም ዋንጫ አስተናጋጇ ሃገር መለያ አምራች አሁንም አዲዳስ ሲሆን የ1988 የተባባሩት ሶቪየት ሶሻሊስት ሪፐብሊክ ብሄራዊ ቡድን የለበሰውን ዓይነት የንድፍ መነሻውን አድርጎ በቀይና ነጭ ቀለማት ንድፍ ቅንብር ተዋህዶ የተዘጋጀ ሆኖ በይፋ ቀርቧል። 

የሩሲያ መለያ የ1988 የተባባሩት ሶቪየት ሶሻሊስት ሪፐብሊክ ብሄራዊ ቡድን መለያ ተመሳስሎ የተዘጋጀ ነው

ስፔን

አዲዳስ መለያቸውን ካዘጋጃቸላቸው ሃገራት መካል አንዷ የሆነችው ስፔንም በ2018 ዓለም ዋንጫ የምትለብሰው መለያ የ1994 የዓለም ዋንጫ ተሳታፊ ቡድኗ ለብሶት የነበረውን ዓይነት ተመሳስሎ የተዘጋጀ ነው። 

የ1994 ቡድኗን መለያ መስሎ የተዘገጀው የስፔን መለያ

ስዊዘርላንድ

የስዊዘርላንድ የ2018 ዓለም ዋንጫ መለያ በይፋ በይተዋወቅም በጥቁርና ቀይ ቀለማት የንድፍ ቅንብር ተዋህዶ በፑሜ የተዘጋጀ መለያ ነው።

አርጄንቲና 

የአርጄንቲና መለያም ከአዲዳስ ምርቶች አንዱ ሆኖ ተለምዷዊን የውሃ ሰማያው እና ነጭ የመስመር ቅንብር የያዘ እና የ1993 ብሄራዊ ቡድኗ ለብሶት የነበረውን መለያ ተመሳስሎ የተዘጋጀ ነው። 

የ1993 ብሄራዊ ቡድኗ ለብሶት የነበረውን መለያ ተመሳስሎ የተዘጋጀ የአርጄንቲና መለያ

ብራዚል 

የአምስት ጊዜ የውድድሩ አሸናፊዋ ሃገር መለያ በይፋ ባይተዋወቅም አሁንም በ2018 ዓለም ዋንጫ በናይክ የተዘጋጀው የብራዚል መለያ ፈዘዝና ደመቅ ያሉ ቢጫ ቀለማት ለየት ባለ ሁኔታ በተነፃፃሪ የንድፍ ስልት ተዋህደው ይቅረቡባት እንጂ ከከዚህ ቀድሙ መለያዋ በተለየ ጉልህ ልዩነት ግን የለውም።

ኮሎምቢያ

የኮሎምቢያ መለያም እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ አሁንም በአዲዳስ የተዘጋጀ ነው። ተለምዷዊው ቢጫ፣ ቀይና ጠቆር ያለ ሰማያዊ ቀለም ያለው ነው። 

ሜክሲኮ

አዲሱ የሜክሲኮ የ2018 ዓለም ዋንጫ መለያ ለየት ያለ አቀራረብና ንድፍ ይዞ በይፋ እንዲቀርብ የተደረገ የአዲዳስ ምርት ነው።

ግብፅ

ከአፍሪካ ተሳታፊ ሃገራት ማለፏን ያረጋገጠችው ግብፅ መለያዋን ያዘጋጀው አብዛኛውን የዓለም ዋንጫ ተሳታፊ ሃገረት መለያን ባዘጋጀው አዲዳስ አማካኝነት ነው። 

ጃፓን

ኤዢያን ወክላ ከሚሳተፉ ሃገራት አንዷ የሆነችው ጃፓን በአዲዳስ የተመረተውን ሙሉ ጠቆር የለ ሰማያዊና ነጫጭ ነጠብጠቦች በርከት ብለው የሰፈሩበት መለያ ለብሳ የ2018 የሩሲያ ዓለም ዋንጫ ላይ የምትጫወት ይሆናል።

Advertisements