የርገን ክሎፕ እንግሊዛውያኑ በሚያገኟቸው ውጤታቸው እንዳይረበሹ አሳሰቡ

የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ እንግሊዝ ከጀርመን እና ብራዚል ጋር በምታደርጋቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች በምታገኛቸው ውጤቶች መረጋጋት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የጋርዝ ሳውዝጌት ተጫዋቾች ብዙም ሳይቸገሩ ለ2018 የዓለም ዋንጫ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። ነገር ግን ለሩሲያው ውድድር ብቁ ስለመሆናቸው ጉዳይ ግን ከወዲሁ ጥያቄዎች መነሳት ጀምረዋል።

እንግሊዝ ከሁለቱ የዓለም ምርጥ ሃገራት ጀርመንና ብራዚል ጋር እንደቅደም ተከተላቸው በዌምብሌይ የወዳጅነት ጨዋታዎችን በማድረግ ትፈተናለች።

ይሁን እንጂ ክሎፕ እንግሊዝ በእነዚህ ውጤቶች ልትመዘንባቸው እና የሳውዝጌቱ ቡድን ስኬታማ ነበር ወይም አይደለም ሊባልባቸው የሚችልባቸው ምክኒያቶች እንደሌሉ ተናግረዋል።

“የወዳጅነት ጨዋታዎችን ማደረግ ስትፈልግ ከጀርመን ሌላ ቡድን ብትመርጥ ይሻልሃል። እና ደግሞ ብራዚልን በሁለተኝነት ይህ የምር የሚያስቅ ነው።” ሲሉ ጀርመናዊው አሰልጣኝ ለእንግሊዙ ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ ሃሳባቸውን ገልፀዋል።

“ሁሉም ጋዜጠኞች መረጋጋት ይኖርባቸዋል። እና ደግሞ ብዙ መጠበቅ አይኖርባቸውም። በእርግጥ ማሸነፍ ስለማይችሉ አይደለም። ነገር ግን ቢያሸንፉ በጣም ትልቅ ነገር ታደረጉታላችሁ። ቢሸንፉም አንዲሁ። 

“ማጣሪያው እንደተጠናቀቀ ሰዎች አሁን ችግሩ መጀመሩን ይናገራሉ። ምክኒያቱም ውድድሩ እየተቃረበ ነው። እንግሊዝ ደግሞ በርካታ ድንቅ ወጣት ተጫዋቾች አሏት። እውነታው ያ ነው።

“ጀርመን ምን አይነት አሰላለፍ እንደምትጠቀም እርግጠኛ አይደለሁም። ነገር ግን በእርግጠኝነት ጥሩ ጨዋታ ይሆናል። ሆኖም ጫዋታው ስለመጪው ጊዜ ምልክት ይሆናል ብዬ ግን አልናገርም።” 

Advertisements