የጣሊያን ወደዓለም ዋንጫ አለማለፍ “ትራጄዲ” እንዳልሆነ ሬይሞንድ ዶሜኔክ ተናገሩ

ሬይሞንድ ዶሜኔክ ጣሊያን ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ አለመቻሏ “ትራጄዲ” እንደማይሆን ተናግረዋል።

በ2006 የዓለም ዋንጫ የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድንን በአሰልጣኝነት እየመሩ በፍፃሜው በመለያ ምት በጣሊያ ሽንፈት የገጠማቸው የ65 ዓመቱ አሰልጣኝ ዶሜኔክ ስለአዙሪዎቹ አስተያየታቸውን እንዲሰጡ በጣሊያኑ ጋዜጣ ጋዜታ ዴሎ ስፖርት ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። 

“ጣሊያ  ከሌለች ትራጂ የለም? ይህ ለእናንተ ሊሆን ይችላል። ለዓለም ግን እንደዚያ አይደለም። ዓለም አርጄንቲናን የማጣት አደጋ ውስጥም ገብቶ ነበር።” ሲሉ ለጋዜጣው ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

“ጣሊያን ታልፋለች? በእርግጠኝነት። 2006ን ተመልከቱ ይህ ዓይነቱ ችግር ነበረባችሁ። ነገር ግን አሸንፋችኋል። 

“ጣሊያን ጭንቀትን እንዴት መወጣት እንደሚኖርባቸው የሚያውቁ ተጫዋቾች አሏት። የስዊዲን ግን ዝቅተኛ ነው። ከምድባቸው ለማለፍ ተቀርበው ነበር። ነገር ግን ህይወት ውስብስብ ነበረች። 

“ቡፎን? ታለቅ ተጫዋች ነው። በ2006 የወርቅ ጓንት አሸናፊ አለመሆኑ ጥፋት ነው። አሁንም ድረስ ከምርጥ ግብ ጠባቂዎች መካከል አንዱ ነው። አሁንም በ40 ዓመት ዕድሜው ጥሩ ነው። ነገር ግን ይህ ከእሱ የሚጠበቅ ነው።

“የጣሊያን ምርጥ ተጫዋቾች? ምናልባት ቦኑቺና ባርዛግሊ። እሱ [ቦኑቻ] በጣም ጥሩ ተጫዋች ነው። በአሰልጣኝነት ዘመኔ የገጠምኩት ምርጥ ተጫዋች? ጥያቄድ ከባድ ነው። ነገር ግን ቡፎን፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ…[ኸቪየር] ሳቪዮላም በጣም ጥሩ ተጫዋች ነው።

“ስለ2006 የፍፃሜ ጨዋታ የምናወራ ከሆነ ማቴራዚ። ግብ አስቆጥሯል፤ ዚዳንን በቀይ ካርድ አሰናብቷል፤ እንዲሁም ፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል። እሱ በጣም ምርጥ ነበር። 

“ፒርሎ? ድንቅ ተጫዋች ነበር፤ ነገር ግን በእሱ ዘመን ምርጡ ጣሊያናዊ አልነበረም። ከ21 ዓመት በታች ቡድን ውስጥ ሲጫወት ገጥሜዋለሁ። ግብ በማስቆጠር የ2000 ኦሎምፒክን ወርቅ አሳጥቶኛል።

“ይሁን እንጂ ወደመሃል የቀየረውን አንቸሎቲን ማመስገን አለበት። እሱ እጅግ ምጡቅ 10 ቁጥር አልነበረም።

“ጨዋታ ከማንበብ ችሎታው አንፃር ጥሩ አሰልጣኝ መሆን ይችላል። ቬራቲን እና ባሎቴሊን እወዳቸዋለሁ? ቫራቲን አዎ።

“ባሎቴሊ ለብሄራዊ ቡድኑ ሲጫወት ከምርጦቹ አንዱ ነበር። ፈጣንና ጥሩ አድርጎ ኳስ አክርሮ መምታት ይችላል። ነግር ግን አንዳድን ጊዜ ይቆምና የቡድን አጋሮቹን ብቻ ይመለከታል።

“በቪዲዮ የታገዘ ዳኝነት ዚዙ በማታሬዚ በጭንቅላት ለተመታበት ድርጊት ያስፈልግ ነበር? ውሳኔው ትክክል ነበር። ነገር ግን ቪዲዮን መጠቀም ትክክል አይደለም። 

“ህግ ካለ ለሁሉም ተግባራዊ መሆን አለበት አበለዚያ ተግባራዊ መሆን የለበትም። የዓለም ዋንጫን የማንሳት ዕድል ያላቸው? ብራዚል፣ ጀርመን እና ስፔን።”

Advertisements