ፈረንሳዊው ላውረንት ኮሺሊኒ ከአለም ዋንጫ በኋላ ከብሔራዊ ቡድኑ ጫማውን እንደሚሰቅል አሳወቀ

​ፈረንሳዊው የመድፈኞቹ ተከላካይ ላውረንት ኮሺልኒ ከ2018 የአለም ዋንጫ በኋላ ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ጫማውን እንደሚሰቅል አሳውቋል።

የመድፈኞቹ ተከላካይ ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በሶስት ትላልቅ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ በአጠቃላይ በ 49 ጨዋታዎች ላይ የአገሩን ማሊያ መልበሰ ችሏል።

ነገርግን ከ ስድስት ወራት በኋላ የሚጀመረው የ2018 የአለም ዋንጫ ሀገሩን ወክሎ የሚሳተፍበት የመጨረሻው ውድድር እንደሚሆን አሳውቋል።

“ሁሉም ነገር ፍጻሜ አለው።ከአለም ዋንጫ በኋላ 33 አመት ይሆበኛል፣ስለዚህ ቦታውን መልቀቅ የሚገባኝ ጊዜ ነው።ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ጋር ለመለያየት ስድስት ወራት ይቀረኛል።በመቀጠል ከኔ በኋላ ላሉ ወጣቶች ቦታውን መልቀቅ ይኖርብኛል። ከቡድኑ ጋር የምፈልገውን እንዳደረኩኝ አስባለው፣እስከ  ሰኔ ድረስም ከቡድኑ ጋር ልረሳቸው የማልችላቸው ትዝታዎችን ለማሳለፍ እድሉ አለኝ።”ሲል ሀሳቡን ሰጥቷል።

32 ተኛ አመቱ ላይ የሚገኘው ተከላካይ የመጀመሪያውን ጨዋታ ለሀገሩ ያደረገው 2011 ላይ ሲሆን በዩሮ 2012፣በዩሮ 2016 እንዲሁም በ 2014 የአለም ዋንጫ ላይ የብሔራዊ ቡድኑ አባል ነበር።

በ2016 የአውሮፓ ዋንጫ ላይም ፈረንሳይ እስከ ፍጻሜ ደርሳ ሳይጠበቅ በፖርቹጋል ተሸንፋ የዋንጫ እድሏን አሳልፋ ስትሰጥ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ዋንጫ ለማንሳት የተጠጋበት የውድድር አመት ነበር።

ተጫዋቹ ምንም እንኳን ከሀገራዊ ጨዋታዎች እራሱን እንደሚያገል ቢያሳውቅም በክለብ ተሳትፊው ግን እንደሚቀጥል ጨምሮ ተናግሯል።

“ከፊትለፊቴ የምጫወትበት ጥቂት አመቶች አሉ።”ሲል የክለብ ቆይታውን ለተወሰኑ አመታት እንደሚቀጥል አሳውቋል።

በፈረንሳይ ወጣት ተጫዋቾች መምጣት እራሱን ያረጀ አይነት ስሜት ተሰምቶት መሆኑን ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ “ለሁሉ ነገር ፍጻሜ አለው ያ ደግሞ ጤናማ አካሄድ ነው።”ሲል ይገልጸዋል።

ለአለም ዋንጫ ማለፍ የቻለችው ፈረንሳይ ህዳር ወር ላይ ከጀርመን እና ከዌልስ ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ታደርጋለች።

Advertisements