“በዚነዲን ዚዳን ስር መሰልጠን እፈልጋለሁ ” – ኤደን ሃዛርድ

​በተደጋጋሚ የክርስቲያኖ ሮናልዶ ተተኪ ሆኖ ወደሳንቲያጎ በርናባው ከመምጣት ጋር ስሙ የሚያያዘው ቤልጅየማዊ የቼልሲ ኮከብ ኤደን ሃዛርድ በማድሪዱ አሰልጣኝ ዚዳን ስር የመስራት ፍላጎት እንዳለው በመግለፅ ጭምጭምታውን ዳግም ቆስቁሶታል፡፡

<!–more–>

በሰማያዊዎቹ ቤት ቁጥር አንድ ኮከብ የሆነው ሃዛርድ በአለም አቀፍ ጨዋታዎች ምክንያት ከቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚገኝ ሲሆን በአልቫሮ ሞራታ መልቀቅ ፣ ከካሪም ቤንዜማና ክርስቲያኖ ሮናልዶ የቀድሞ አቋም ላይ አለመገኘት ተከትሎ የአጥቂ ክፍሉ የተዳከመውን ሪያል ማድሪድን ማንቂያ ደወል ሊሆነው የሚችል አስተያየት ሰጥቷል፡፡

ተጫዋቹ ሲናገር ” ለዚዳን ያለኝን አመለካከትና ፍቅር ሁሉም ያውቃል ፤ በተጫዋችነት ዘመኑም ሆነ አሁነ ባለበት የአሰልጣኝነት ጊዜው እጅግ የማከብረውን ስራ ሰርቷል፡፡ በተጨማሪም አረአያዬ ነበር፡፡ ወደፊት ምን ሊፈጠር እንደሚችል ባላውቅም በሱ ስር መስራት ግን ህልሜ ነው ” ብሏል፡፡

ተጫዋቹ በተጨማሪም አሁን ላይ ሙሉ ትኩረቱን በሰማያዊዎቹ ላይ ማድረጉን የተናገረ ሲሆን ከቀድሞ አሰልጣኙ ጆዜ ሞሪንሆ ጋር በድጋሚ አብሮ የመስራት ችግር እንደሌለበት አሳውቋል፡፡

Advertisements