ቼልሲ የተጫዋቾቹን ጸጉር አስተካካይ ወደ ልምምድ ቦታ እንዳይገባ ያገደበት አስገራሚ ምክኒያት

8.jpg

የቼልሲ ተጫዋቾችን ጸጉር በማሳመር ይሰራ የነበረው አህመድ አልሳናዊ በአስገራሚ ምክኒያት ወደ ኮብሀም የልምምድ ማእከል እንዳይገባ  ክለቡ አግዶታል፡፡

አህመድ አልሳናዊ በቼልሲ ልምምድ ማእከል እየተገኘ እንደ ዲያጎ ኮስታ፣ጋሪ ካሂል፣ዴቪድ ልዊዝ፣ሴስክ ፋብሪጋዝ፣ኤደን ሀዛርድ እና የሌሎች ከክለቡ ከዋክብቶችን ፀጉር እያሳመረ ባለፉት አመታት ቆይቷል።ተጫዋቾቹ በፈለጉት አይነት ፀጉራቸውን እያሳመረ ስራውንም እያሳደገ ሄዷል፡፡

ፀጉር አስተካካዩ በክለቡ ማእከል እየተገኘ ከተጫዋቾቹ ጋር ፎቶ መነሳትን ልማድ አድርጎት ቆይቷል፡፡በስራው ላይም የእነዚህ ኮከብ ተጫዋቾችን ፀጉር እየሰራ በሰልፊ ፎቶ ሲነሳ ይታያል፡፡

አህመድ አልሳናዊ ከክለቡ ጋር ቅራኔ የገባበት እና በክለቡ የልምምድ ማእከል ድርሽ እንዳይል የታገደበት ምክንያትም ከዚሁ ከምስል መብት ጋር የተያያዘ መሆኑ አስገራሚ አድርጎታል፡፡

7

ፀጉር አስተካካዩ ከተጫዋቾቹ ጋር ፎቶ እየተነሳ ስራውን ለማስፋፋት ምስላቸውን ማስታወቂያ እያደረገ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየለቀቀ ቢዝነሱን ሞቅ አድርጎታል።የተጫዋቾቹን ምስል እየተመለከቱ ሌሌች ባለሀብቶችም እሱ ጋር ጸጉራቸውን መሰራት ጀምረዋል፡፡

በኮብሀም ልምምድ ማእከል አቅራቢያም ጸጉር ቤት በመክፈት እንደነ ፖል ፖግባ አይነት ለጸጉራቸው የሚጨነቁ ደንበኞችን ማፍራት ችሏል፡፡በኢንስታግራም ገጹም ላይ ከ 73 ሺ በላይ ተከታይ ማፍራት ችሏል።

የምስል መብት ጥያቄ እንዲሁም ተጫዋቾቹ በየማህበራዊ ሚዲያዎች ጸጉራቸውን ሲሰሩ የሚያሳየውን ምስል መለቀቁን ያልወደደው ቼልሲ ፀጉር አስተካካዩን ከአሁን በኋላ በኮብሀም እንዳይገባ አግዶታል፡፡ከተጫዋቾቹ ጋር ያለው ደምበኝትም አብቅቷል፡፡

 

 

 

Advertisements