ከሀገራዊ ጨዋታዎች በኋላ በአስገራሚ ብቃት እንደሚመለስ ልዊስ ስዋሬዝ ተናገረ

የጎል መንገዱ የጠፋበት ልዊስ ስዋሬዝ ከኢንተርናሽናል ጨዋታዎች በኋላ በሙሉ ብቃቱ አስደናቂ ሆኖ እንደሚመለስ ተናግሯል።

30 አመቱ ላይ የሚገኘው ኡራጋዊው አጥቂ በጉልበት ጉዳት እና በአቋም መውረድ ምክኒያት ከአስራ አራት ጨዋታዎች ሶስት ጎሎችን ብቻ ማስቆጠሩ እየተተቸ ይገኛል።

ተከላካዮችን በመረበሽ ይታወቅ የነበረው የፊት መስመር አስፈሪነቱ ዘንድሮ አብሮት የሌለለ ሲሆን ለኤርኔስቶ ቫልቬርዴው ባርሴሎናም አዲስ ያልለመደ ተጫዋች መስሏል።

ተጫዋቹ ሰሞኑን ኡራጋይ የምታደርጋቸው ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ላይ የማይሳተፍ በመሆኑ አቋሙን አስተካክሎ ለመመለስ ጥሩ አጋጣሚ እንዳገኘ አስቧል።

ወደ ክለብ ጨዋታዎች እስኪመለስ ድረስ ያሉት የሁለት ሳምንታት ጊዚያቶች ወደ ብቃቱ ጫፍ ላይ እንዲመለስ አጋጣሚውን እንደሚፈጥሩለት እምነቱ አለው።

“በነዚህ ሁለት ሳምንታት እረፍት ወስጄ እና በደንብ አገግሜ በአስደናቂ ብቃት እመለሳለው።ጉዳት ካጋጠመኝ በኋላ ከጉልበት ጉዳቴ ጋር እየታገልኩ ነበር።ነገርግን ቆየት ሲል ህመም ይሰማሀል።በብሔራዊ ቡድንም ስለምሳተፍ በአካል ብቃቴ ላይ ትንሽ ጫና ነበረብኝ፣እስካሁን ድረስም ምንም አይነት እረፍት አላገኘሁም።

“ትልቁ ነገር ከክለቤ እና ከ ኡራጋይ ብሔራዊ ቡድን ጋር ነገሮችን ማመቻቸት ነው።ከፓላንድ እና ኦስትሪያ ጋር የምናደርገው የአቋም መፈተሻ ጨዋታም እንድጫወት የመመረጥ ቅድሚያ አላገኝም።”ሲል ምላሹን ሰጥቷል።

የጉልበት ጉዳቱ ምክንያት አሁን የሚሰማው ነገር እንዳለ የተጠየቀው ስዋሬዝ “በፍፁም፣በፍፁም .. ጥሩ ምቾት ግን አይሰማኝም።ሁልጊዜ ግጭት አጋጥሞህ ህመሙ ይበልጥ እንዳይባባስ ትፈራለህ፣ነገርግን ከዚህ እረፍት በኋላና እየሰራሁት በሚገኘው የክትትል ስራዎች ምክንያት ወደ ሜዳ ስመለስ ምንም አይነት ህመም ሊሰማኝ አይችልም። ” ሲል ጨመሮ አሳውቋል።

ስዋሬዝ ምንም እንኳን የሚጠበቅበትን ያህል ጎል ማስቆጠር ባይችልም ክለቡ ባርሴሎና ግን በምርጥ አጀማመር ላሊጋውን እየመራ ይገኛል።በተለይ ከባላንጣው ሪያል ማድሪድ በስምንት ነጥብ በልጦ በተረጋጋ ሁኔታ ላይ ተቀምጧል።

Advertisements