“ከክርስቲያኖ ጋር አልስማም።” – ራሞስ

ሰርጂዮ ራሞስ ሪያል ማድሪድ በዝውውር መስኮቱ ወቅት ሳንቲያጎ በርናባውን የለቀቁ ተጫዋቾችን ማጣቱ እንደጎዳው ባቀረበው የመከራከሪያ ሃሳብ እንደማይስማማ ገልፅዋል።

ፔፔ፣ አልቫሮ ሞራታ እና ኻመስ ሮድሪጌዝ ማድሪድ ከ2017-18 የውድድር ዘመን በፊት ከክለቡ ከቀነሳቸው ተጫዋቾች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። እናም ክለቡ በ11 ጨዋታዎች የላ ሊጋውን መሪ፣ ባርሴሎናን በስምንት ነጥቦች ርቆ በመከተል አስቸጋሪ የውድድር ዘመን ጅማሮ አድርጓል።

ነገር ግን ሮናልዶ ማድሪድ የውጤት ማጣት ትግል ውስጥ የገባው  እንደጋርዝ ቤል እና ራፋኤል ቫራን ያሉ ተጫዋቾችን በጉዳት ማጣቱን እንደማሳያ በመጠቀስ የሰጠውን አስተያየት አጣጥሎታል። 

“ከክርስቲያኖ ጋር አልስማም።” ሲል ፔፔ ለስፔኑ ሚዲያ ካዴና ሰር ተናግሮ “ይህ የተገኘውን አጋጣሚ የሚጠቀሙ ሰዎች አስተያየት ነው።” ብሏል።

“ሁለት የሱፐር ካፕ [የአውሮፓ ሱፐር ካፕ እና የስፔን ሱፐር ካፕ] ዋንጫዎችን ስናነሳ ማንም ሰው እነሱን አላጣቸውም ነበር።

“ለጉዳቶች ከፍ ያለ አፅንኦት አሰጣለሁ። ሁላችንም በአንድ ላይ ስንሆን ቡድኑ ጠንካራ ነው።

“እኔ ግን ማንንም አላጣሁም። ማንንም።

“እርግጥ ነው የቡድን ስብስቡ ለውጥ አድርጓል። ነገር ግን የአንዳንዶች አስተዋፅኦ በአንድ ነገር ላይ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ ሌላ ሚና አላቸው።” ሲል ስፔናዊው ተጫዋች ተናግሯል።

ሮናልዶ በዚህ የውድድር ዘመን ባደረጋቸው ሰባት የሊግ ጨዋታዎች ላይ ማስቆጠር የቻለው አንድ ግብ ብቻ ነው።

“ማንም ቢያስቆጠር ግድ አይሰጠኝም። ለእኔ የደስታ ስሜቱ አንድ ዓይነት ነው።” ሲል ራሞስ አክሎም ተናግሯል።

“ነገር ግን እሱ [ሮናልዶ] የተለየ ሚና አለው። አንተ በምታስቆጥራቸው አይነት ግቦች ላይ ጥገኛ የሚሆኑ በአንድ ግለሰብ ላይ የተንጠለጠሉ በርካታ የዋንጫ ድሎች አሉ።” 

Advertisements