የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የክረምቱ ዝውውር መስኮት ፈራሚ ስኬታማ ተጫዋቾች 

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የክረምቱ የዝውውር መስኮት ክለቦች ለአዲሱ የውድድር ዘመን ስኬታቸው ሲሉ በዝውውር መስኮቱ ላይ እንደአቅማቸው ተሳትፎ አድርገው ተጫዋቾችን ሸምተዋል። ኢትዮአዲስ ስፖርትም እስካሁን በተካሄዱት የውድድር ዘመኑ የሊጉ ጨዋታዎች ከብራይተን ዝቅተኛ ወጪ እስከ ማንችስተር ሲቲ ዳጎስ ያለ ወጪ ድረስ የተደረጉ ስኬታማ የተጫዋቾች ግዢዎችንና በሊጉ ላይ ያሳዩትን የግዢ ፍሬያማነት እንደሚከተለው ቃኝታቸዋለች።

ፓስካል ግሮስ (ከኢንጎልሽታድ ወደ ብራፕተን በ2.6ሚ.ፓ)

ብራይተኖች ግሮስን ከጀርመኑ ክለብ ኢንጎልሽታድ ለማምጣት የከፈሉትን ክፍያ ፍሬ ከወዲሁ በሚገባ ማየት ችለናል። ክሪስ ሁቶን በዚህ የውድድር ዘመን ብዙ የሜዳ ላይ ርቀቶችን ሸፍነው መጫወት ከቻሉ ስምንት ተጫዋቾች (በዚህ ዝርዝር ውስጥ ከአንድ በላይ ተጫዋች ማካተት የቻሉ ክለቦች የሉም) መካከል ሶስቱን በቡድናቸው ውስጥ በማካተት ታታሪ ቡድን ገንብተዋል። ግሮስ ደግሞ በዚህ ኃይልኛ ጉልበት ያለው ተጫዋች ነው። የውጤት አምራችነቱንም በቆሙ ኳሶች እና በነፃ አጨዋወት ላይ በሚያሳድረው ተፅእኖ ማሳየት ችሏል። ብራይተኖች 11 የሊግ ግቦችን ማስቆጠር የቻሉ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከልም ግሮስ ሁለቱን ሲያስቆጥር አምስት የግብ ዕድሎችን ደግሞ መፍጠር ችሏል። ግሮስ ባልተጫወተባቸው እስከ ጥቅምት 10 ድረስ ባሉት ጊዜያት ብራይተን ግብ ማስቆጠር አልቻለም ነበር።

አሮን ሙይ (ከማንችስተር ሲቲ ወደኸደርስፊልድ ታውን በ8ሚ.ፓ)


ሙይ ያዳረጋቸው 574 ቅብብሎሽ ከኸደርስፊልድ ተጫዋቾች ሁሉ በሰፊ ልዩነት(ከእሱ ቀጥሎ ክርስቶፎር 416 ኳስ ሲያቀብል፣ በመቀጠል ደግሞ በ415 ኳሶች ማቲያስ ዛንካ ተቀምጧል) ተፅእኖ ፈጣሪ እንዲሆን አስችሎታል። ከክለቡ አጋሮቹ የትኛቸውም በላቀም ኳስን ተንሸራቶ መንጠቅም ችሏል። ከሊጉ ተጫዋቾችም በዚህ የውድድር ዘመን በዚህ ተግባር የሚበለጠው በሌሰተሩ ዊልፍሬድ ንዲዲ ብቻ ነው። ያስቆጠራቸው ሁለት ግቦችም በክለቡ በጥምር ክፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን እንዲመራ አስችሎታል። ተጫዋቹ ባለፈው የውድድር ዘመን በኸደርስፊልድ በውሰት ይጫወት እንጂ በቋሚነት ለመጫውት ግን ፊርማውን ያኖረው በክረምቱ ነበር። የኸደርስፊልዱ አሰልጣኝ ዳቪድ ዋግነር ስለተጫዋቹ ሲናገሩም “አሮን የቡድናችን የልብ ትርታ ነው። አስፈላጊ ሲሆን ጨወታውን ያቀዘቅዘዋል። አስፈላጊ ሲሆን ዳግሞ ጨዋታውን ያፈጥነዋል። ብዙ ጊዜ እንደእሱ አይነት በኳስ ቁጥጥር ሂደቱ ላይ ዘና ያለና እና በራስ መተማመን እንዲሁም የተፋላሚነት ባህሪ ያለው ተጫዋች አታገኝም።” ብለዋል።

ሞ ሳላህ (ከሮማ ወደሊቨርፑል በ36.9ሚ.ፓ)

በፕሪሚየር ሊጉ ባደረጋቸው 11 ጨዋታዎች ላይ ካስቆጠራቸው ሰባት ግቦች በተመጨማሪ በአራት የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ላይ አራት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። እንዲሁም ሃገሩ ግብፅ ከኮንጎ ጋር ባደረገችው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች ለተሳታፊነት አብቅቷል። ምንም እንኳ በወሳኝ ጨዋታዎች ላይ ግቦችን በማምከን (ለምሳሌ በማንችስተር ሲቲ ጨዋታ መጀመሪያ ላይ እና በኸደርስፊልድ ላይ የሳተው ፍፁም ቅጠት ምት ይጠቀሳሉ) ቢታወስም ያስቆጠራቸው ግቦች የቁጥር መረጃ ግን ትልቅ ዋጋ የሚያሰጠው ነው። ግብ ለማስቆጠር ያገኛቸው የግብ ዕድሎች ወደግብ የመቀየር ልኬቱም 6.18 ግቦች ናቸው። ምንም እንኳ በአጠቃላይ ሙከራዎች በአራተኛ ደረጃ ላይ ቢገኝም፣ ከየትኞቹም በፕሪሚየር ሊጉ ላይ ከሚጫወቱ ተጫዋቾች በላይ ግን ዒላማቸውን የጠበቁ የግብ ሙከራዎችን ማድረግ ችሏል። ባደረጓቸው የግብ ሙከራ ጥረቶች 37 በመቶውን መረብ ላይ ማስረፍ ከቻለው ሃሪ ኬን እና 47 በመቶውን መረብ ላይ ማሳረፍ ከቻለው ሮሜሉ ሉካኩ ጋር ሲነፃፀርም የእሱ የግብ ስኬት 65 በመቶ ነው። በሊቨርፑል ቆይታቸው በዚህ ጊዜ ውስጥ ፈርናንዶ ቶሬስም ሆነ ልዊስ ስዋሬዝ የእሱን ያህል ግብ ከመረብ ላይ ማሳረፍ አልቻሉም፤ በዚያ ላይ ሁለቱም ተጫዋቾች አጥቂዎች እንጂ የክንፍ ተጫዋቾች አልነበሩም።

ካይሊ ዎከር (ከቶተንሃም ወደማንችስተር ሲቲ በ50ሚ.ፓ)

“ካይሊ ዎከር በ50 ሚሊዮን ፓውንድ እና ተጨማሪ ክፍያ የዓለማችን ውዱ ተከላካይ ሆነ።” ሲል የቀድሞው የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች ጋሪ ሊንከር የተጫዋቹ ስምምነት እንደተጠናቀቀ በትዊተር ገፁ ላይ ፅፎ ነበር። “ኳሶችን ማሻማት ቢችል ኖሮ ደግሞ ምን ያህል ሊያወጣ እንደሚችል አስቡት።” ሲልም የቀድሞው ዝነኛ ተጫዋች በፅሁፉ ላይ አክሎ ነበር። ያነሳው ነጥብ አሳማኝ ነጥብ ይመስላል። ምክኒያቶም በቶተንሃም የአምስት ዓመታት ቆይታው ምንም እንኳ አማካኝ ኳስ የማሻማት ቁጥሩ 85 ቢሆንም በሊጉ በየውድድር ዘመኑ አማካኝ ግብ የማመቻቸት ቁጥሩ 2.8 ነበር። በዚህ የውድድር ዘመን ግን ከወዲሁ 20 ኳሶችን ሲየሻማ አራት የግብ ዕድሎችን ደግሞ መፍጠር ችሏል። ይህ ማለት ደግሞ ካሻማቸው አምስት ኳሶች አንዱ ወደግብ ተቀይሯል ማለት ነው። በሊጉ ካሉ የግብ ፈጣሪ ተከላካይ ተጫዋቾች ዝርዝር ላይም (ከቶተንሃሙ ኪራን ትሪፐር ጋር በእኩል ደረጃና እንዲሁም ከቼልሲው ሴዛር አዝፒሊኩዌታ ቀጥሎ) በሁለተኛነት ተቀምጧል። ከተለየዩ ቦታዎች ላይ ኳስን ማሻማት መቻሉ ደግሞ ያን ያህል ስኬታማ እንዲሆን አስችሎታል። ይህ ብቻም ሳይሆን ግን እንግሊዛዊው ተጫዋች በቡድኑ ላይ የሚቃጡ የጥቃት ሙከራዎችንም በመመከት ከፍተኛ ድርሻ አለው።

ሪቻርሊሰን (ከፍሉሚኔንሴ ወደዋትፎርድ በ11ሚ.ፓ)

ሪቻርሊሰን ልምድ አልባ ተጫዋች በመሆኑ ኸርትፎርድሻየር ሲደርስ የብዙዎችን ትኩረት ያልሳበ ቢሆንም ዋትፎርዶች ግን በብራዚለዊው ተጫዋች ላይ ከፍተኛ ተስፋ ጥለውበት ነበር። “በአውስትራሊያ በነበርንበት ጊዜ [በቅድመ የውድድር ዘመን] ሙሉውን ጨዋታ ተመልክተን የተጫዋቹን ጥሩነት ስለመረዳታችን አስታውሳለሁ።” ሲሉ ማርኮ ሲልቫ መሰከርም ወር ላይ ተናግረው “እናም በወቅቱ ውሳኔ ላይ ደረስኩና ከቦርዱ ጋር ስገናኝ ‘ይህን ተጫዋች መግዛት የግድ ይለናል።” አልኳቸው። ሲልቫ ለተጫዋቹ ስልክ በመደወል የኃሳብ ለውጥ እንዲያደርግ ከማሳመናቸው በፊት ተጫዋቹ አያክስን ለመላቀል ወደአምስተርዳም በረራ ለማድረግ ሰዓት ብቻ ነበር የሚቀሩት። የ20 ዓመቱ ተጫዋች ተፅእኖ ፈጣሪነቱን ለማሳየት በውድድር ዘመኑ የመጀመሪያ ጨዋታ ከተቀያሪ ወንበር ላይ ተነስቶ መጫወት ብቻ ነበር ያስፈለገው። በዚያ ጨዋታ ላይ መጫወት የቻለው ለ10 ደቂቃዎች ያህል ብቻ የነበረ ቢሆንም ፍጥነቱ፣ አብዶው እና ያለስስት የሚያዳረጋቸው የግብ ጥረቶችቹ በጥምረት ድንቅ ነበሩ። የቷሟላ ኳስን በሚገባ ተቆጣጥሮ የማንሸራሸር እንቀስቃሴው በአሁኑ ጊዜ በሊጉ በስድስተኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥ አስችሎታል። እስካሁንም ለክለቡ አራት ግቦች የማስቆጠርና ሶስት የግብ ዕድሎችን የመፍጠር አስተዋፅኦ ማደረግ ችሏል።

Advertisements