“የኔይማር ወደ ፈረንሳዩ ፒ ኤስ ጂ ማቅናት ለኔ ምቾት ሰጥቶኛል”- ጆርዲ አልባ

የባርሴሎናው የግራ ተከላካይ የሆነው ጆርዲ አልባ ኔይማር ባርሴሎናን ለቆ ወደ ፒ ኤስ ጂ ማቅነቱ ለሱ ትልቅ ጥቅም እንደሰጠው አሳወቀ።

ስፔናዊው የቀድሞ የቫሌንሺያ የግራ እግር ተጫዋች የሆነው ጆርዲ አልባ በባርሴሎና ቆይታው በግራ መስመር ላይ ድንቅ እንቅስቃሴ በማድረግ ይታወቃል።

አራት አመት ከካታላኑ ቡድን ጋር ስኬታማ ቆይታ ያደረገው ኔይማር በበኩሉ ውጤታማ ቆይታ ያደረገ ሲሆን ለቡድኑ ስኬትም ጉልህ ሚና መጫወት ችሏል።

ኔይማር ከክለቡ ሳይወጣም አልባ ከብራዚላዊው ጀርባ በመሆን የግራ ኮሪደሩን ሁለቱ አንድ ላይ በመሆን በማጥቃቱ ረገድ አስፈሪ አድርገውት ያለፉት አመታት አሳልፈዋል።

ኔይማር በማጥቃቱ ላይ በአብዛኛው መሳተፉ ለስፔናዊው የግራ እግር ተጫዋች በመከላከሉ ረገድ ላይ ትኩረቱን አብዝቶ ሰብስቦ ለመጫወት በመገደዱ መስመሩን ይዞ ወደፊት በነጻነት ለማጥቃት ሳይችል ቀርቷል።

ነገርግን የ25 አመቱ ብራዚላዊው ክለቡን ከለቀቀ በኋላ ጆርዲ አልባ በግራ ኮሪከር ላይ በቂ የመጫወቻ ቦታ በማግኘቱ የኔይማርን ከክለቡ መልቀቅ በመልካም ጎኑ ተመልክቶታል።

ከሙንዶ ዲፓርቲቮ ጋር ቆይታ ያደረገው ጆርዲ አልባ “ኔይማር አስደናቂ ተጫዋች ነው።በራሱ ፍላጎትም ክለቡን ለመልቀቅ ወስኗል።የሱ መልቀቅ ግን እኔን ጨምሮ ብዙ ተጫዋቾች ስራቸውን በጥሩ ሁኔታ እንዲሰሩ አድርጓቸዋል።

“ከዚህ ቀደም እንዳልኩት በግራ መስመር ላይ ብዙ የመሮጫ ቦታ በማግኘቴ ለኔ የሱ መልቀቅ በጣም ተስማምቶኛል።ለረጅም አመታት ያላገኘሁት በመሆኑ አሁን የራስ መተማመኔንም መልሼ ማግኘት ችየበታለው።” ሲል በኔይማር ከክለቡ መልቀቅ መጠቀሙን አሳውቋል። 

Advertisements