ሙኒር ቼልሲ ሊያሰፈርመው ሙከራ አድርጎ እንደነበረ ገለፀ

ቶማስ ሙኒር ቼልሲ በዝውውር መስኮቱ መዝጊያ የመጨረሻ ቀን ከፒኤስጂ ሊያስፈርመው ሙከራ አድርጎ እንደነበር ገልፅዋል።

ፒኤስጂ ኡናይ ኤምሬ በክለቡ የቀራቸው ብቸኛ ልምድ ያለው የቀኝ መስመር ተጫዋቹ ሙኒር መሆኑን ተከትሎ ቤልጂየማዊው ተጫዋች ፓርክ ደስ ፕሪንሰስን እንዲለቅ ፈቃደኛ አልነበረም።

በቼልሲ ሲፈለግ ቆይቶ ሰማያዊዎቹ ዛፓኮስታን በ23 ሚሊዮን ፓውንድ በማስፈረማቸው ምክኒያት ቶተንሃምን በ23 ሚ.ፓ መቀላቀል ምርጫው ያደረገውን ሰርጌ ኦሪየር በዝውውር መስኮቱ የመጨረሻ ቀን ፒኤስጂን እንዲለቅ ተፈቅዶለታል።

ቼልሲ በዝውውር መስኮቱ የመጨረሻ ቀን ለባየር ሙኒኩ የቀን መስመር ተከላካዩ ራፊንሃም (ተጫዋቹ በጀርመኑ ሻምፒዮን መቆየትን ምርጫው በማድረጉ) ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ተደርጎበታል።

“በዝውውር መስኮቱ የመጨረሻ ቀን እነሱ (ቼልሲዎች) ለፒኤስጂ ጥያቄ አቅርበው ነበር። ነገር ግን [መልሳቸው] አይሆንም እንደሆነ አውቀው ነበር።” ሲል ሙኒር ቤልጂየም በወዳጅነት ጨዋታ ከሜክሲኮ ጋር 3ለ3 ከተለያየች በኋላ ከስካይ ስፖርትስ ኒውስ ጋር ባደረገው ቆይታ ተናግሯል።

“ክለቡ ሊሸጠኝ አልፈለገም ነበር። ምክኒያቱ የነበርነውም ዳኒ አልቬስ እና እኔ ሁለት የቀኝ መስመር ተጫዋቾች ነበርን። ከሁለት አንዳችንን መሸጥ ደግሞ አስቸጋሪ ነበር።

“የእውነት ግን እኔ [ቼልሲን መቀላቀሉን] አላስበኩበትም ነበር። ምክኒያቱም ‘አንተ አትሄድም። ስለዚህ ስለቼልሲ ወይም ስሌላ ክለብ አታስብ። በፓሪስ ትቆያለህ። በውድድር ዘመኑ ሁለንም የጣልነው በአንተ ላይ ነው።’ ለማለት ደውለውልኝ ነበር።” ሲል ተጫዋቹ ወደቼልሲ ለመዛወር ያልቻለበትን ምክኒያት ገልፅዋል።

Advertisements