በኢትዮጵያ እግር ኳስ እስካሁን ያልታዩት አወዛጋቢው ሰው አቶ ተክለወይኒ አሰፋ

Image may contain: 1 person

በለፈለፉ በአፍ ይጠፉ የሚለው ብሂል አቶ ተክለ ወይኒ አሰፋ ላይ ሰርቷል፡፡ በሳምንቱ አጋማሽ በመላው ኢትዮጵያ መነጋገሪያ አጅንዳ ሆነው የሰነበቱት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝደንት በመጨረሻም አዳልጧቸው በተናገሩት ጸያፍ ቃል የትግራይ ክልል ካሁን በኋላ ውክልናዪን አንስቻለው  በቃኝ በማለት ውክልናቸውን ማንሳቱን ይፋ አድርጓል፡፡

ዘመኑን የጨረሰው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን  ከ4 አመታት  በፊት ስልጣኑን ከአቶ ሳሕሉ ገብረወልድ አስተዳደር ሲረከብ ወደ ሚዲያው ብቅ ያሉት አቶ ተክለ ወይኒ አሰፋ በወቅቱ ልብ ያላቸው ባይኖርም አወዛጋቢ አስተያየቶችን በእግር  ኳስ ፌዴሬሽኑ ዙሪያ በመስጠት የጥቂቶች መነጋገሪያ ሆነው ሰንብተዋል፡፡

በተለይም የቀድሞውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የምንግዜም ውጤታማ አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻውን ፌዴሬሽኑ በ2005 ዓ.ም ከአሰልጣኘነት ሲያነሳ አስተያየታቸውን የሰጡት አቶ ተክለ ወይኒ አሰፋ በወቅቱ የኢትዮጵያ እግር ኳስን ከስፔን ከብራዚል እና እንግሊዝ ጋር በማነጻጸር አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻውን  ፌዴሬሽኑ ለማባረር መወሰኑን ተናግረው የበርካቶች ማሾፊያ ሆነው ነበር፡፡

አምባገነን እንደሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ተክለወይኒ አሰፋ በእግር ኳስ ፍቅር እንደተለከፉ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቢደመጥም በ4 አመታት የስልጣን ዘመናቸው ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ይህ ነው ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል በጎ ተግባር ሳይከውኑ በመጨረሻም በሚሰጥዋቸው አነጋጋሪ አስተያየቶች ምክንያት የትግራይ ክልል ውክልናዪን አንስቻለው ሲል ሸኝቷዋል፡፡

ይህንንም ተክትሎ መብቴን ለማስከበር እና ወደ ቀድሞ ቦታዮ ለመመለስ እስከ ፍርድ ቤት እሄዳለው ያሉት ቆፍጣናው የቀድሞ ታጋይ የህግ ባለሙያዎቸን በማነጋገር ላይ እንደሚገኙ ተሰምቷል፡፡ ሆኖም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ዳግም አቶ ተክለወይኒ አሰፋን ላያይ ከወዲሁ ተሰናብቷቸዋል፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ እጅግ የወረዱ የሌሎችን ስብሕና ዝቅ የሚያደርጉ አስተያየቶችን የሰጡት አቶ ተክለወይኒ አሰፋ ባሳለፍነው  ሀሙስ ጅማሮውባደረገው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽም ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ሰብስበሳው  መቐለ ቢካሄድ ጥሩ ነው፣ ማታ ማታ ከትግራይ ቆነጃጅት ጋር ዘና ትላላችሁ የሚል አስተያየትን በመስጠት በርካቶችን ያስቆጡ ሲሆን

በሳምንቱ አጋማሽ ደግሞ ለኢትዮ ስፖርት በሰጡት አስተያየት “እኔ የድርጅቴ ሲኒዬር ስትራቴጅስት እኮ ነኝ፣ ሃይለማሪያም ምን ያውቃል፣ ከፈለገ አምጣውና እንከራከር፣ አናስተምረዋለን”  ብለዋል፡፡ በዚህ ብቻ ያላበቁት አቶ ተክለ ወይኒ የኢትዮጵያ ቡና ክለብ የቦርድ ሊቀመንበር የሆኑትን  መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞን ደግሞ በጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ መሃል “አንተ አደናቃፊ ሰውዬ ዝምበል” አዛውንቱን አለቃ ያስከፋ ንግግር ተናግረዋል፡፡

 

Advertisements