ሳዲዮ ማኔ ጉዳቱ አገርሽቶበት ወደአንፊልድ ተመለሰ

ሳዲዮ ማኔ በቅርቡ ገጥሞት የነበረው የቋንጃ ጉዳቱ ዳግም ያገረሸበት በመሆኑ ከብሄራዊ ግዳጁ በቶሎ ወደሊቨርፑል እንዲመለስ መደረጉን የሴኔጋል እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

የ24 ዓመቱ የፊት መስመር ተጫዋች በጥር ወር ለሴኔጋል በመጫወት ላይ እያለ በገጠመው የቋንጃ ጉዳት አንድ ወር ለሚጠጋ ጊዜ ከሜዳ ርቆ ነበር።

ማኔ ሙሉ በሙሉ ከጉዳቱ አገግሞ እ.ኤ.አ. ህዳር 4፣ 2017 ሊቨርፑል  ዌስት ሃምን 4ለ1 ማሸነፍ በቻለበት ጨዋታ ላይ ተሰልፎ መጫወትም ችሏል።

ይሁን እንጂ የሴኔጋል እግርኳስ ፌዴሬሽን ተጫዋቹ ጉዳቱ ዳግም ስላገረሸበት ከሊቨርፑል የህክምና ቡድን አባላት ጋር ከተወያየ በኋላ ለህክምና ክትትል ወደመርሲሳይድ እንዲመለስ የፈቀደለት መሆኑ በሰጠው መግለጫ ገልፅዋል። 

ማኔ ከብሄራዊ ግዳጁ ውጪ ከመሆኑ በፊት ሴኔጋል ደቡብ አፍሪካን 2ለ0 በመርታት ከ16 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዓለም ዋንጫ ተሳትፎ እንድትበቃ ቁልፍ ሚና መጫወት ችሎ ነበር።

የተጫዋቹን የጉዳት ደረጃ አስመልክቶ ግን የሴኔጋል የእግርኳስ ፌዴሬሽንም ሆነ ክለቡ ሊቨርፑል ያሉት ነገር የለም።

Advertisements