በባርሴሎና የሚፈለገው ኮቲንሆ በሊቨርፑል የመቆየት ፍላጎት እንዳለው ፍንጭ ሰጠ

ፊሊፔ ኮቲንሆ ለሀገሩ፣ የብራዚል ጋዜጠኞች አሁን ባለው ህይወቱ “በጣም ደስተኛ” መሆኑን በመናገር በሊቨርፑል የመቆየት ፍላጎት ያለው መሆኑ አመላክቷል።

የ25 ዓመቱ ተጫዋች በነሃሴ ወር በካታላኑ ታላቅ ክለብ የቀረበለት የዝውውር ጥያቄ በሊቨርፑል ውድቅ በመደረጉ ዝውውሩ ተቀባይነት እንዲያረኝ ቢጠይቅም ነገር ግን ቀዮቹ የእሱን ጥያቄ ከቁብ ሳይቆጥሩ ተጫዋቹ የማይሸጥ መሆኑን በይፋ በመግለፅ ለሁለት ጊዜያት የቀረቡላቸውን የዝውውር ጥያቄዎች ሳይቀበሉ ቀርተዋል።

ኮቲንሆም በውድድር ዘመኑ መጀመሪያ ገጥሞት ከነበረው ጉዳት ካገገመ በኋላ ዳግም ከቡድኑ ጋር ስኬታማ ጥምረት ማድረግ ችሎ ይገኛል። ምንም እንኳ ያለፉት ሶስት ጨዋታዎች ላይ በስር መዞር ጉዳት  መሰለፍ ባይችልም ብሄራዊ በድኑ ከእንግሊዝ ጋር በሚያዳርገው የወዳጅነት ጨዋታ ላይ ግን ለመሰፍ ዝግጁ ሆኖ ይገኛል።

“ከዓለማችን ታላላቅ ሊጎች መካከል በአንዱ ውስጥ በመጫወት ላይ እገኛለሁ።” ሲል ኮቲንሆ ለስካይ ስፖርትስ ተናግግሮ “ሁልጊዜም ደስተኛ ነኝ። ነገር ግን አሁን በብሄራዊ ቡድን ጨዋታዎች ላይ ትኩረቴን ማድረጌ ፋይዳ አለው። በአሁኑ ጊዜ በህይወቴ በጣም ደስተኛ ነኝ።

“ሁልጊዜ ራሴን ለማሻሻልና ከእግርኳስ ተጫዋቾች ሁሉ የተሻልኩ ለመሆን ይበልጥ ጠንክሬ እየሰራሁ ነው።” በማለት ገልፅዋል።

ክለቡ ሊቨርፑልም ኮቲንሆ ዳግም ወደሙሉ ብቃቱ በመመለሱ ዜና ደስተኛ እንደሚሆን ይጠበቃል። 

“እንዳለመታደል ሆኖ በጉዳት ምክኒያት ለሊቨርፑል ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ላይ መሰለፍ አልቻልኩም።” ሲልም ጨምሮ ተናግሯል።

“አሁን መቶ በመቶ በሙሉ ብቃት ላይ የመገኘት ስሜት ይሰማኛል። አገግሜያለሁ። ከእንግሊዝ ጋር ለምናደረገው ጨዋታም በጥሩ አቋም ላይ እገኛለሁ። 

“ፈፅሞ የትኛውም የብራዚል ጨዋታ እንዲያልፈኝ አልፈልግም። በተቻለኝ አቅም ሁሉ ይህን መለያ ስለብስ ክብር ይሰማኛል።”