ሪቫልዶ ማንችስተር ዩናይትድ ሊያስፈርመው ሙከራ አድርጎ እንደነበር ገለፀ

የቀድሞው የባርሴሎና ኮከብ ሪቫልዶ ማንችስተር ዩናይትድ ሊያስፈርመው ፍላጎት አሳይቶ እንደነበር ሆኖም ዝውውሩን ለማጠናቀቅ የሚያስችለው ዕድል ግን ፈፅሞ እንዳልቀረበለት ገልፅዋል።

ብራዚላዊው ተጫዋች በ1997 ከዲፖርቲቮ ላ ካሩኛ ባርሴሎናን ከተቀላቀለ በኋላ የካታላኑን ክለብ በተከታታይ ዓመታት የላ ሊጋ ዋንጫ አሸናፊ እንዲሆንና አንድ የኮፓ ዴል ሬይ ዋንጫን ማንሳት እንዲችል ማደረግ ችሏል።

ሪቫልዶ በ2002 ለኤሲ ሜላን ከመሸጡ በፊትም በባርሴሎና ለአምስት ዓመታት ቆይታ አድርጓል። ነገር ግን ወደሴሪ ኣው ከማምራቱ በፊት ወደእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሊያመራ ነው የሚሉ ወሬዎች በሰፊው ሲናፈሱበት ቆይተው ነበር።

“በእርግጥ በባርሴሎና በነበርኩበት ወቅት ባርሴሎና ወደእንግሊዝ ሊያዛውረኝ እያሰበበት እንደነበር በርካታ ወሬዎች ይወሩ ነበር። ነገር ግን ፈፅሞ ዕድሉን አላገኘሁትም።” ሲል ሪቫልዶ ለ2017 ቤት ሴፍ ስታር ሲክስስ ተናግሯል።

“በባርሴሎና ውስጥ ያሉ ሁሉም ጋዜጦች በርካታ ወኪሎች ከእኔ ጋር ሲነጋግሩ እንደነበር የሚገልፁ የጭምጭምታ ወሬዎችን ፅፈዋል። ምን ያህል እውነት እንደነበሩ ግን አላውቅም። ነገር ግን ጋዜጦቹ ማንችስተር ፈላጊዬ ክለብ እንደነበር ገልፅዋል። እኔ ይህ ምን ያህል እውነት እንደነበር ግን አላውቅም። ወሬው የጋዜጦቹ ነበር።” ሲል ገልፅዋል።

ሪቫልዶ በ2002 በጀፓኑ የዓለም ዋንጫ ከብራዚል ጋር የዓለም ዋንጫን ከማንሳቱ ባሻገር በ2002-03 የውድድር ዘመን ከኤሲ ሚለን ጋር የሻምፒዮንስ ሊግን ዋንጫ በማሸነፍ በቶሎ ስኬታማ ጊዜን ማሳለፍ ችሏል።

ይሁን እንጂ የ45 ዓመቱ የቀድሞ ተጫዋች የባሎን ዶር ሽልማትን ባገኘበት ባርሴሎና ትልቅ ስኬትን እንዳገኘ ይናገራል።

“[እ.ኤ.አ] በ1999 የዓለም ምርጡ ተጫዋች ተብዬ እውቅና ተሰጠኝ። ይህ ደግሞ ትልቅ ፋይዳ ነበረው።” ሲል ሪቫልዶ ተናግሮ አክሎም “የተገኘሁት አስገራሚ ከሆነ ደሃ ቤተሰብ ነበር። እናም ምርጥ ተጫዋችነት ደረጃ ላይ መድረሴም የሚገርም ነው።” ሲል ገልፅዋል።

የምንጊዜውም ምርጥ አምስት ተጫዋቾችን እንዲመርጥ ጥያቄ የቀረበለት ሪቫልዶ አብረውት ከተጫወቱ ተጫዋቾች ሁሉ ማንን መምረጥ እንዳለበት እንደሚቸግረው ገልፃ “ይህ በጣም አስቸጋሪ ነው። በአዕምሮዬ ላይ ከአምስት በላይ ተጫዋቾች አሉ። በዚህ ዝርዝር ውስጥ ያላካተትኳቸው ግን እንደማይናደዱበኝ ተስፋ አለኝ።

“እሺ ግብ ላይ ዲዳ፣ ፑዮል፣ ፊጎ፣ ሮናልዶ፣ ሮናልዲንሆ፣ ዚዳን፣ ሪቫልዶ።” በማለት ብራዚላዊው ምርጫውን ገልፅዋል።

Advertisements