ናትናኤል ክላይን ለተጨማሪ ሶሰት ወራቶች ከሜዳ ይርቃል

እንግሊዛዊው የሊቨርፑል የቀኝ መስመር ተካላካይ ናትናኤል ክላይን ለተጨማሪ ሶስት ወራቶች ከሜዳ እንደሚርቅ ተረጋግጧል፡፡ ከጉዳቱ ለማገገም ቀዶ ጥገና ያደረገው ክላይን እስከ የካቲት ወር ድረስ ወደ ሜዳ እንደማይመለስ የታወቀ ሲሆን ከጉዳቱ  ሙሉ በሙሉ እስኪድንም በሊቨርፑል ማገገሚያ ማዕከል እንደሚቆይ ተሰምቷል፡፡

ቀለል ያሉ ልምምዶችን ከወርሀ መስከረም ጀምሮ በግሉ ሲከውን የሰነበተው የ26 አመቱ ናትናኤል ክላይን ከቀዶ ጥገናው በፊት የርገን ክሎፕ ጥሩ መንገድ ላይ ነው በቅርብ ይመለሳል ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን ተጫዋቹ ግን ጉዳቱ አግርሽቶበት ለተጨማሪ ሶሶት ወራት ከሜደ መራቁ እርግጥ ሆኗል፡፡

በቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት ሊቨርፑል ከትራንሜር ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ ጉዳት የገጠመውን ናትናኤል ክላይን  የቀኝ መስመር ቦታም  ጆይ ጎሜዝ እና አሌክሳንደር አርኖልደ  በመሸፈን ላይ ይገኛሉ፡፡ ቀዮቹ በሳምንቱ መጨረሻ በአንፊልድ ሮድ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሳውዝአምፕትን ጋር ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን ከወዲሁም ከመሪው ማንችስተር ሲቲ በ12 ነጥቦች ዝቅ ብለው በደረጃ ሰንጠረዡ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

Advertisements