የስፔን ላሊጋ የቪዲዮ አሲስታንስ ሪፈሪን በቀጣይ አመት ለመሞከር አቅዷል

Premier League officials were put through VAR training last month

የስፔን ላሊጋ በቀጣዩ አመት የቪዲዮ አሲስታትት ሪፈሪን የመጀመር እቅድ መያዙን የስፔን ላሊጋ ፕሬዝደንት ሀቪየር ቴባስ ተናግረዋል፡፡ከአምስቱ ታላላቅ የአውሮፓ ሊጎች የስፔን ላሊጋ እስካሁን የጎል ላይን ቴክኖሎጂን ሳይጠቀም ቢሰነብተም በቀጣይ አመት ግን ከሁሉም ሊጎች ቀደም ብሎ የቪዲዮ አሲስታትት ሪፈሪን የመሞከር ውጥን መያዙን ፕሬዝደንቱ ይፋ አድርገዋል፡፡

የጎል ላይን ቴክኖሎጂ ኳስ መስመር ማለፏን ብቻ ለዳኛው ይፋ በማድረግ ምን አልባት ዳኛው ያላስተዋላቸውን ግቦች እንዲያጸድቅ የሚያስችል የዘመነ ቴክኖሎጂ ሲሆን የቪዲዮ አሲስታትት ሪፈሪ ደግሞ የተቆጠሩ ግቦች ቀይ ካርዶች ኦፍሳይዶች ፋውሎች እና በጨዋታ መሀል የሚፈጠሩ ስዕተቶችን የሚቆጣር ሲስተም ነው፡፡

የቪዲዮ አሲስታትት ሪፈሪ በ2017 የሩሲያው ኮንፌዴሬሽን ካፕ ላይ ተግባራዊ ሆኖ በበርካቶች ትችት የደረሰበት ሲሆን የእግር ኳሱን ውበት ያደበዝዛል በሚልም በርካቶች የቪዲዮ አሲስታትት ሪፈሪ በሌሎች ውድድሮች ላይ ተግባራዊ እንዳይሆን ሲከላከሉ ሰንብተዋል፡፡

ባሳለፍነው አመት ባርሴሎና እና ሪያልቤትስ ባደረጉት ጨዋታ በባርሰሎና በኩል በግልጽ መረቡን አልፋ የተቆጠረች  ኳስ ሳትቆጠር መቅረቷን ተከትሎ ላሊጋው የጎል ላይን ቴክኖሎጂን እንዲጠቀም በስፔን ክለቦች የተወተወተ ሲሆን ከጎል ላይን ቴክኖሎጂው ቀደም ብሎም  የቪዲዮ አሲስታትት ሪፈሪን ለመጠቀም ወስኗል፡፡

የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበርም በቅርቡ በሚደረጉ የተመረጡ የኤፍ ኤካፕ  እና የኢፍኤል ካፕ ጨዋታዎች ላይ የቪዲዮ አሲስታትት ሪፈሪን ለመሞከር ማቀዱ ይታወሳል፡፡ ከዚህ ቀደምም የጀርመን የጣሊያን የፖርቱጋል ሊጎች የቪዲዮ አሲስታትት ሪፈሪን በይፋ መጠቀም የጀመሩ ሀገሮች ሲሆኑ በ2018 የሩሲያ የአለም ዋንጫም ይህ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 

Advertisements