ሀቪየር ማሻራኖ በጉዳት ምክንያት ለ2 ወራት ከሜዳ ይርቃል

የmascherno argentina ምስል ውጤት

የባርሴሎናው አርጀንቲናዊው ኮከብ ሀቪየር ማሻራኖ በደረሰበት የብሽሽት ጉዳት ምክንያት ለ 2 ወራት ከሜዳ እንደሚርቅ ተረጋግጧል፡፡ ሀገሩ አርጀንቲና ከናይጄሪያ ጋር ባደረገቸው  በአቋም መፈተሻ ጨዋታ ላይ ጉዳቱ የገጠመው የ33 አመቱ  ተከላካይ ጉዳቱን ተከትሎ ባርሴሎና በቀጣይ እስከ ገና መዳረሻ በሚያደርጋቸው የሻምፒየንስ ሊግ እና የላሊጋ ጨዋታዎች ላይ የማይሰለፍ ይሆናል፡፡

የባርሴሎናው ተከላካይ  በሩሲያ ተደርጎ በነበረ እና ናይጄሪያ አርጀንቲናን 4-2 በረታችበት ጨዋታ ላይ የቀኝ እግሩ ላይ የብሽሽት ጉዳቱ የገጠመው ሲሆን በፍጥነትም ወደ ባርሴሎና በመመለስ ምርመራ ማድረጉ ተነግሯል፡፡ ለወራት ከሜ እንደሚርቅ የተነገረለት ሀቪየር ማሻራኖ ባርሴሎና በኤል ክላሲኮ ሪያል ማድሪድን በሚገጥምበት ጨዋታ ሊመለስ እንደሚችል ከወዲሁም እየተነገረ ይገኛል፡፡

የካታላኑ ክለብ በላሊጋው እና በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ስኬታማ ጉዞን እያደረገ እንዲገኝ ካስቻሉ ኮከቦች አንዱ የሆነው አርጀንቲናዊው ኮከብ ከመጎዳቱ ቀደም ብሎም ባርሴሎና ላሊጋውን በ31 ነጥቦች እየመራ የሚገኝ ሲሆን ከ2ኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጠው ቫለንሲያም 4 ነጥቦች ርቆ ይገኛል፡፡

 

 

Advertisements