አስደንጋጭ / የርገን ክሎፕ በህመም ምክንያት በልምምድ ሜዳ ሳይገኙ ቀሩ

Reds boss Jurgen Klopp admitted himself to hospital after feeling unwell

ጀርመናዊው የሊቨርፑል አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በህመም ምክንያት ዛሬ ረፋድ በሜልውድ የልምምድ ማዕከል ሳይገኙ ቀርተዋል፡፡ የ50 አመቱ አለቃ የህመም ስሜት ከተሰማቸው በኋላ ወደ ሆስፒታል ማቅናታቸው የተነገረ ሲሆን በህመሙ ምክንያትም ጥሪ ያልሆነ ስሜት ስለተሰማቸው በዛሬው ልምምድ ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል፡፡

ከኢንተርናሽናል ጨዋታ መልስ ሁሉም የሊቨርፑል ተጫዋቾች በዛሬ የልምምድ ፕሮግራም ላይ በሜልውድ የታደሙ ቢሆንም ልምምዳቸውን ግን ያለ ጀርመናዊው አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ለመከወን ተገደዋል፡፡ ክለቡ በኦፊሻል ድረ ገጹ ላይ እንዳሳወቀውም ክሎፕ በህመም ምክንያት ወደ ዶክተር ጋር እንዳቀኑ ያሳወቀ ሲሆን ስለ ህመማቸው እና ዝርዝር ጉዳዮች ግን ምንም ነገር ከማለት ተቆጥቧል፡፡

ባሳለለፍነው ሳምንት ለበጎ አድራጎት ስራ ወደ ደቡብ አፍሪካ አቀንተው የነበሩት የሊቨርሉ አለቃ የርገን ክሎፕ ቅዳሜ ክለባቸው ከሳውዝአምፕተን ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ላይ ቡድናቸውን ይምሩ አይምሩ የታወቀ ነገር ባይኖርም እስከ ቅዳሜ አገግመው በአንፈልድ ሮድ የሜዳው ጠርዝ ላይ ቀዮቹን እንደሚመሩ ይጠበቃል፡፡

 

Advertisements