አስገራሚ / አሜሪካ ከሩሲያው የዓለም ዋንጫ ውጪ የሆኑ ታላላቅ አገራትን የሚያሳትፍ ውድድር ልታዘጋጅ ነው


አሜሪካ ከ 2018 የሩሲያ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ውጪ የሆኑ  ታላላቅ የእግር ኳስ አገራት የሚሳተፉበት ውድድር የማዘጋጀት ውጥን መያዟ ተሰምቷል፡፡

የአራት ጊዜ የአለም ዋንጫ ሻምፒዮኗን ጣልያን ጨምሮ በርካታ ትልልቅ ቡድኖች የአለም ዋንጫ ተሳትፎን ማሳካት የተሳናቸው ሲሆን ከነዚህ አገራት አንዷ የሆነችው አሜሪካም እነዚህን አገራት በሌላ ውድድር የማሳታፍ ዕቅዷን ለመተግበር እንቅስቃሴ እንደጀመረችና በፌዴሬሽኗ አማካኝነት ከአገራቱ ጋር ግኑኝነት እንደፈጠረች ተሰምቷል፡፡

ከጣልያንና ከአሜሪካ በተጨማሪ ሌላኛዋ ማጣሪያውን ማለፍ የተሳናት አውሮፓዊት ታላቅ የእግር ኳስ አገር ኔዘርላንድም የዚህ ውድድር ተሳታፊ እንድትሆን ጥረት እንደተጀመረ ያወራው ዴይሊ ሜይል በደቡብ አሜሪካ ማጣርያው ያልተሳካላት ቺሊም ብሔራዊ ቡድኗን ልታሳትፍ እንደምትችል ዘግቧል፡፡

ዘገባው ጨምሮም ውድድሩ በመጪው ክረምት ሊካሄድ እንደታሰበ ጠቅሶ ፣ የአለም ዋንጫው በሚካሄድበት ወቅት በተመሳሳይ ጊዜ ለማካሄድ ከታሰበ ግን ፊፋ ውድድሩን የሚያግድበት ዕድል እንደሚኖር አትቷል፡፡

Advertisements