የሩሲያ የአለም ዋንጫ 31 ተሳታፊ ሀገራት ተለይተዋል

የ2018 world cup ምስል ውጤት

የ2018 የአለም ዋንጫ በሩሲያ አስተናጋጅነት ሊጀመር ወራት ቀርተውታል ፡፡ በዚህ የአለማችን ታላቁ የእግር ኳስ ውድድርም ከወዲሁ 31 ሀገራት ወደ አለም ዋንጫው የሚውስዳቸውን ትኬት የቆረጡ ሲሆን  ዛሬ ለሊት ፔሩ እና ኒዋዚላንድ በሚያደርጉት የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታም 32ኛዋ ሀገር የምትታወቅ ይሆናል፡፡

በታህሳስ መጀመሪያ በሞስኮ በሚወጣው የምድብ ድልድልም በወርሀ ሰኔ ጅማሮውን የሚያደርገው የአለም ዋንጫ ተሳታፊ ሀገራት የምድብ ተጋጣሚዎቻቸውን እንደሚለዩ ይጠበቃል፡፡ በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ለወራት ተፋልመው ለታላቁ ውድድር እስካሁን ማለፋቸውን ያረጋገጡ 31 ሀገራት ከስር በየአህጉራቸው እንደሚከተለው ከስር ቀርበዋል፡፡

አውሮፓ

አለም ዋንጫውን የተቀላቀሉ የአውሮፓ ሀገራት:

 • ሩስያ  (አዘጋጅ)
 • ቤልጂየም
 • ጀርመን
 • እንግሊዝ
 • ስፔን
 • ፖላንድ
 • አየስላንድ
 • ሰርቢያ
 • ፖርቱጋል
 • ፈረንሳይ
 • ስዊዘርላንድ
 • ክሮሸያ
 • ስዊዲን
 • ዴንማርክ

ኤሽያ  

አለም ዋንጫውን የተቀላቀሉ የኤሽያ ሀገራት:

 • ኢራን
 • ጃፓን
 • ደቡብ ኮሪያ
 • ሳውዲ አረቢያ
 • አውስትራሊያ

አፍሪካ

አለም ዋንጫውን የተቀላቀሉ የአፍሪካ ሀገራት:

 • ናይጄሪያ
 • ግብጽ
 • ሴኔጋል
 • ሞሮኮ
 • ቱኒዚያ

ኮንካፍ

አለም ዋንጫውን የተቀላቀሉ የሰሜን መካከለኛው እና የካረቢያን ሀገራት:

 • ሜክሲኮ
 • ኮስታሪካ
 • ፓናማ

 

ኮንቦሜል

አለም ዋንጫውን የተቀላቀሉ የደቡብ አሜሪካ ሀገራት:

 • ብራዚል
 • ኡራጋይ
 • አርጀንቲና
 • ኮሎምቢያ

ኦሺኒያ

አለም ዋንጫውን የተቀላቀሉ የደቡብ አሜሪካ ሀገራት:

የማለፍ ተስፋ ያላቸው ሀገራት የደቡብ አሜሪካዋ ተወካይ ፔሩ ከኦሺኒያዋ ተወካይ ኒውዝላንድ ጋር ባደረገቸው የመጀመሪያ ጨዋታ 0-0 በሆነ ውጤት የተለያየች ሲሆን የመልሱን ጨዋታ መርታት የቻለ ሀገር በቀጥታ 32ቱን ሀገራት መቀላቀል ይችላል፡፡

 

Advertisements