“የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ከሌሎች ሀገራት በተለየ ይከላከላል” ኔይማር ጁኒየር

Neymar and Brazil could not find a way past England in Tuesday's friendly at Wembley

ባሳለፍነው ማክሰኞ ምሽት እንግሊዝ እና ብራዚል በዌምብሌይ ካደረጉት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ በኋላ በጋሬዝ ሳውዝጌት የሚመሩት እንግሊዞች ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን ያለግብ ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ብሄራዊ ቡድኑ መከላከልን መሰረት አድርጎ እየተጫወተ ነው ተብሎ በበርካቶች ወቀሳ እየተሰነዘረበት ይገኛል፡፡ የአለማችን ውዱ ተጫዋች ብራዚላዊው ኔይማር ጁኒየርም የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን በጣም ተከላካይ ቡድን ነው ሲል የሶስቱ አናብስትን  አጨዋወት መንገድ ተናግሯል፡፡

“በጨዋታው ግቦችን ለማስቆጠር የተቻለንን ብንጥርም የእንግሊዞች የመከላከል አጨዋወት ግብ እንዳናስቆጥር አድርጎናል፡፡ ኳሱን ተቆጣጠርን ወደ እነርሱ ግብ ክልል እንድንደርስ እድል አልሰጡንም እነርሱ ከሌሎች ሀገራት በተለየ ይከላከላሉ ”በማለት ከጨዋታው በኅላ የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ምን ያህል በጨዋታው ላይ መከላከልን ምርጫው አድርጎ እንደገባ አብራርቷል፡፡

የብራዚል ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቲቴም ከኔይማር ጋር የተመሳሰለ አስተያየት የሰጡ ሲሆን “አየሩ እጅግ ቀዝቃዛ ነበር በዚህ ቅዝቃዜ ትኩረታችንን አለማጣታችን መልካሙ ነገር ነው፡፡ በዚህ አመት በርካታ ግቦች እያስቆጠርን ብናሸንፍም በዚህ ጨዋታ ግብ ማስቆጠር ተስኖናል ምክንያቱም ደግሞ እነርሱ ተከላክለው መጫወታቸው ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የደቡብ አሜሪካ ማጣሪያዋን በአንደኛነት ካጠናቀቀች በኋላ  ለ2018 የአለም ዋንጫ ከወዲሁ የማሸነፍ ቅድመ ግምትን እያገኘች የምትገኘው ብራዚል በቅደመ ማጣሪያው ካደረጋቸቻቸው 18 ጨዋታዎች መሀል በ አስራ ሁለቱ ድል ያደረገች ሲሆን በአንዱ ብቻ ተሸንፋ በቀሪዎቹ 5 ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይታለች፡፡

Advertisements