ሹመት/ ካርሎ አንቸሎቲ የጣሊያን ብሄራዊ ቡድን አዲሱ አሰልጣኝ ለመሆን ተቃርበዋል

Sky Sports News understands that Ancelotti has been approached by the Italian Football Federation

ጂያንፒሮ ቬንቹራን የሸኘው የጣሊያን ብሄራዊ ቡድን ከባየርሙኒክ የአሰልጣኝነት መንበራቸው ባሳለፍነው ወር የተነሰቱን ካርሎ አንቸሎቲን ለመሾም ስለመቃረቡ ከወደ ጣሊያን የሚሰሙ መረጃዎች እያመለከቱ ይገኛሉ፡፡ የቀድሞ የኤስ ሚላን አለቃም  አንቸሎቲም ጂያንፒሮ ቬንቹራን ተክተው የአዙሪዎቹ አሰልጣኝ የመሆናቸው እድልም የሰፋ ሆኗል፡፡

እንደ ታማኙ ዴሉ ስፖርት ዘገባ ከሆነም የጣሊያን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሰዎች ከወዲሁ ከካርሎ አንቸሎቲ ጋር ድርድር የጀመሩ ሲሆን ለአንድ አመት እረፍት አደርጋለው ያሉትን ጣሊያናዊው ዝምተኛ አሰልጣኝንም ሀሳብ በማስቀየር ብሄራዊ ቡድኑን እንዲመሩ ለማድረግ መቃረባቸውን ምንጮቼ ነግረውኛል ብሏል፡፡

ዘገባው አክሎ እንደገለጸው ከሆነም አንቸሎቲ  እና የጣሊያን እግር ኳስ ማህበር አመራሮች ባሳለፍነው ማክሰኞ ምሽት ተገናኝተው በጉዳዩ ዙሪያ የመከሩ ሲሆን ከስምምነት ለመድረስም በእጅጉ መቃረባቸውን አትቷል፡፡  የ58 አመቱ አለቃን ቅጥር እውን ከሚያደርጉ ነገሮች አንዱም ስመ ጥሩ የአቋማሪ ድርጅት ስካይ ቢት ካርሎ አንቸሎቲ የጣሊያን ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ይሆናሉ ብሎ 4 ላስያዘ 6 ፓውንድ እሰጣለው  ያለ ሲሆን ይህም ከሌሎች ብሄራዊ ቡድኑን ይይዛሉ ተብለው ከሚጠበቁ አሰልጣኞች ከተቀመጠው የማቋመሪያ ሂሳብ ያነሰ ሆኗል፡፡

 

ለጣሊያን ብራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ሹመት የቀረቡት ካርሎ አንቸሎቲ ከዚህ ቀደሞ ለአዙሪዎቹ 26 ጨዋታዎችን በተጫዋችነት ዘመናቸው ያደረጉ ሲሆን አሰልጣኝ ከሆኑ በኋላ ደግሞ ዝነኞቹን  ጁቬንቱስ ኤስሚላን ቼልሲ ፒኤስ ጂ እና ሪያልማድሪድን አሰልጥነዋል፡፡ 3 የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግን ማንሳት የቻሉት የ58 አመቱ አለቃም 2 የሴሪያ ክብሮችን መቀዳጀት ችለዋል፡፡

Advertisements