የሩሲያው ዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ያመለጣቸው 11 ምርጥ ተጫዋቾች

ፔሩ ኒውዚላንድን 2ለ0 በማሸነፍ ከ32 ተሳታፊ ሃገራት ዝርዝር ውስጥ መግባት የቻለች የመጨረሻዋ ሃገር ሆናለች። እናም አሁን በመጪው ክረምት ላይ በሚካሄደው የ2018 የሩሲያ ዓለም ዋንጫ ተሳታፊ የሚሆኑ ሃገራት በሙሉ ተለይተዋል። 

አይስላንድና ፓናማ በክረምቱ ዓለም ዋንጫ በታሪካቸው የመጀመሪያ ተሳትፎ የሚደያደርጉ ሲሆን ሴኔጋልና ግብፅ ደግሞ እንደቅደም ተከተላቸው በውድድሩ ላይ ለሁለተኛ እና ለሶስተኛ ጊዜ ተሳታፊ መሆን የሚችሉበትን ዕድል ማመቻቸት ችለዋል።

ነገር ግን ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ተሳትፎ የነበራቸው በርካታ ሃገራት በውድድሩ ላይ የሚኖራቸውን የተሳትፎ ዕድል ሳያሳኩ ቀርተዋል። ይህ ማለት ደግሞ በብሄራዊ ቡድናቸው ውስጥ የሚጫወቱ ከዋክብት ተጫዋቾቻቸው በየአራት ዓመቱ በሚካሄድው ታላቁ ውድድር ላይ የመሳተፍ ዕድል ሳይኖራቸው ቀርቷል።

የአራት ጊዜ የውድድሩ ሻምፒዮኗ ከአውሮፓዊቷ አቻዋና ታላቋ ሃገር ሆላንድ ጋር ባልተጠበቀ ሁኔታ በውድድሩ ላይ ተሳትፎ ለማድረግ ሳይችሉ የቀሩ ሃገራት ናቸው።

እንዲሁም ኦስትሪያ፣ ዌልስ እና ቼክ ሪፐብሊክም ለሁለት ዓመታት ሲካሄድ በቆየው ማጣሪያ ላይ ሲቸገሩ ቆይተው በመጨረሻም የተሳትፎ ዕድሉን ማሳካት ያልቻሉ ቡድኖች ናቸው።

በሌላ በኩል ከአውሮፓ ሃገራቱ በተጨማሪ እንደቺሊ፣ አሜሪካ እና አልጄሪያ ያሉ ቀደምት የተሳትፎ ታሪክ የነበረቻው ነገር ግን ለዘንድሮው ውድድር ማለፍ ሳይችሉ የቀሩ ሃገራትም አሉ።

እኛም ከታላላቆቹ ሃገራት የሩሲያውን የዓለም ዋንጫ ውድድር መቀላቀል ካልቻሉ ተጫዋቾች መካከል 11 ምርጥ ተጫዋቾን እንደሚከተለው ተመልክተናቸዋል።

ግብጠባቂ፣ ጂያንሉጂ ቡፎን (ጣሊያን)

ለሃገሩ 175 ጨዋታዎች ላይ መሰለፍ የቻለው ጣሊያናዊው ግብ ጠባቂ በስዊዲን በደርሶንመልስ ውጤት 1ለ0 በመሸነፋቸው በውድድሩ ላይ የመሳተፍ ዕድል ሳያገኝ ቀርቷል። ተጫዋቹ ወዲያውን ከዓለም የእግርኳስ ውድድሮች ላይ ራሱን አግሏል።

የቀኝ ተከላካይ፣ አንቶኒዮ ቫሌንሺያ (ኢኳዶር)

ቫሌንሺያ በውድድሩ ላይ መጫወት ከማይችሉ ምርጥ የደቡብ አሜሪካ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው። ኢኳዶር በማጣሪያው ላይ ከምድቧ በስምንተኛ ደረጃ በማጠናቀቅ የደርሶ መልስ የማጣሪያ ጨዋታ ዕድሏን እንኳ በስድስት ነጥቦች ዝቅ በማለት አጥታለች።

የመኃል ተከላካይ፣ ሊዮናርዶ ቦኑቺ  (ጣሊያን)

42 ሚ.ዩሮ ዋጋ ያለው ተከላካይ ከስዊዲን ጋር ባደረጉት ጨዋታ ጣሊያ ብዙ ግቦች እንዳይቆጠርባት ማድረድ ቢችልም ወሳኝ በነበረው የመልሱ ጨዋታ ግን ቡድኑ አንድ ግብ ማስቆጠር ባለመቻሉ ማጣሪያውን ማለፍ ሳይችል ቀርቷል። 

የመኃል ተከላካይ፣ ቪርጅል ቫን ዳይክ (ሆላንድ)

የሆላንድ የዓለም ዓቀፍ ውድድሮች አሁንም ውጤት አልባ ሆነው ቀጥለዋል። የአውሮፓውን የጥሎ ማለፍ የደርሶ መልስ ጨዋታ የማጣሪያ ዕድል እንኳ ማሳካት አልቻሉም። ይህ ማለት ደግሞ ቫን ዳይክ ቀጥዩን ክረምት በሙሉ ከሳውዛምፕተን የሚለቅበትን መንገድ ተረጋግቶ የሚያመቻችበት ይሆናል።  

ቀኝ ተከላካይ ዴቪድ አላባ (ኦስትሪያ)

የአላባ ቡድን በማጣሪያው ሰርቢያን፣ አየርላንድንና ዌልስን ተከትሎ ከምድቡ በአስከፊ ሁኔታ አራተኛ ሆኖ አጠናቋል። ክለቡ ባየር ሙኒክ አላባ ለሃገሩ ወደፊት ገፍቶ እንዲጫወት ሲሟገት ቢቆይም የፈለገቱን አንፀባራቂ ብቃት ግን ማሳየት ሳይችልላቸው ቀርቷል።

የተከላካይ አማካኝ፣ ናቢ ኪየታ (ጊኒ)

በቅርቡ የሊቨርፑል ተጫዋች የሚሆነው የአርቢ ሌፕዢጉ ተጫዋች ጊኒን ለዓለም ዋንጫው ማብቃት ሳይችል ቀርቷል። ሃገሩም በማጣሪያ ምድቧ ቱኒዚያን፣ ዲ.ሪ.ኮንጎን እና ሊቢያን ተከትላ በመጨረሻ ደረጃ አጠናቃለች።

የተከላካይ አማካኝ፣ ማርኮ ቬራቲ (ጣሊያን)

በ2018 የዓለም ዋንጫ ውድድር ላይ የመሰለፍ ዕድል ያላገኘው ጣሊያናዊ ከዓለም ምርጥ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው።

የአጥቂ አማካኝ፣ አሌክሲ ሳንቼዝ (ቺሊ)

ወደሩሲያ የማያመራ ምርጥ ደቡብ አሜሪካዊ ተጫዋች ነው። ሳንቼዝ በማጣሪያው እንደመሲ ሁሉ ሰባት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። ነገር ግን ቺሊ በግብ ልዩነት በፔሩ ተበልጣ የደርሶ መልስ የጥሎ ማለፍ ዕድሉን እንኳ ማግኘት ሳትችል ቀርታለች።

የአጥቂ አማካኝ፣ ክርስቲያን ፑልሲች (አሜሪካ)

ወጣቱ የዶርትሙንዱ ኮከብ አሜሪካ በትሪንዳድና ቶቤጎ በደርሶ መልስ የጥሎ ማለፍ አዋታው ተሸንፋ ለዓለም አቀፍ ውድድሩ ማለፍ ባለመቻሏ ቅስሙ “እንደተስበረ” ተናግሯል። በመሆኑም የ19 ዓመቱ ተጫዋች በውድድሩ ላይ ኮከብነቱን ማሳየት የሚችልበትን ዕድል አምልጦታል።

የፊት አጥቂ፣ ጋርዝ  ቤል (ዌልስ)

ቤል ዌልስ በደርሶመልሶቹ የጥሎ ማለፍ የማጣሪያ ጨዋታዎች ጎልት እንድትወጣ ማድረግ አልቻለም። በጉዳት ምክኒያትም ወሳኝ በነበረውና በአይርላንድ ሪፐብሊክ 1-0 በተሸነፉበት ጨዋታ ላይም መሰለፍ አልቻለም።

የፊት አጥቂ፡ ፒየር-ኤመሪክ አውባምያንግ (ጋቦን)

የ2015 የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ባሩሲያው ውድድር ላይ አይጫወትም። ምክኒያቱም ጋቦን ከነበረችበት የዓለም ዋንጫው ማጣሪያ ምድቧ በሞሮኮ ተበልጧ ማለፍ ሳትችል ቀርታለች።

Advertisements